Loading
Singer
ነገ ፡ መልካም ፡ ይሆናል እያልኩኝ ፡ በተስፋ ፡ እኖራለሁ ግራ ፡ ቀኝ ፡ አላይም ፡ እጠብቅሃለሁ (፪x) ግን ፡ ለምን ፡ አልገባኝም ስጠራህ ፡ ዝም ፡ አልከኝ የዓይኖቼ ፡ እምባ ፡ እስኪፈስ ለምኜ ፡ ተው ፡ ተመለስ (፪x) በመንፈቅ ፡ ሌሊት ፡ ከአልጋዬ ፡ ወርጄ ሚስጢሬን ፡ ነገርኩህ ፡ ፊትህ ፡ ተደፍቼ እንግዲህ ፡ ሁሉንም ፡ በአድራሻ ፡ ልኬያለሁ እኔም ፡ በአድራሻዬ ፡ እጠብቅሃለሁ (፪x) ከሰዎች ፡ ደብቄ ፡ ለአንተ ፡ የነገርኩህ እንዴት ፡ አደረክልኝ ፡ ያጫወትኩህን ዛሬም ፡ ነገም ፡ እጠብቅሃለሁ ድንገት ፡ ትመጣለህ ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ (፪x) ዓመታት ፡ ሲሄዱ ፡ በጥያቄዬ ፡ ላይ የተውከው ፡ መሰለኝ ፡ ታክቶ ፡ የእኔ ፡ ጉዳይ ዛሬ ፡ ቢሆን ፡ ነገ ፡ እታገስሃለሁ ልትረዳኝ ፡ ስትመጣ ፡ ድንገት ፡ አይሃለሁ (፪x) ከሰዎች ፡ ደብቄ ፡ ለአንተ ፡ የነገርኩህ እንዴት ፡ አደረክልኝ ፡ ያጫወትኩህን ዛሬም ፡ ነገም ፡ እጠብቅሃለሁ ድንገት ፡ ትመጣለህ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ (፪x) አይሃለሁ ፡ ስትደርስልኝ አይሃለሁ ፡ ስትመጣልኝ አይሃለሁ ፡ መልሴንም ፡ ከላይ አይሃለሁ ፡ ስትልክልኝ (፫x)