Loading
Singer
እሱ ፡ ትልቅ ፡ ሆኖ ፡ ትንሽ ፡ አላስብም ማመስገኔን ፡ ትቼ ፡ አላጉረመርምም ይሆናል ፡ እንዳለኝ ፡ ይሆናል ፡ እላለሁ ተስፋውን ፡ እየሰጠሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው ታማኝ ፡ ነዉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው (፬x) እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሆናል እንዳሰበው ፡ ሁሉ ፡ ይፈጸማል ያደርገዋል ፡ ብዬ ፡ ተደግፌዋለሁ እንደተናገረኝ ፡ ይሆናል ፡ አምናለሁ ይሰራዋል ፡ ብዬ ፡ ተደርፌዋለሁ እንደተናገረኝ ፡ ይሆናል ፡ አምናለሁ በእርሱ ፡ ስራ ፡ ጣልቃ ፡ አልገባም ፡ እግዚአብሔር ፡ ልክ ፡ ነው እስማማለሁ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ባይገባኝም ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ለእኔ ፡ ቢሆን ፡ ግራ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል ፡ ልቁም ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ትክክል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ትክክል ፡ ነው (ትክክል ፡ ነው) ትክክል ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ትክክል ፡ ነው (ትክክል ፡ ነው) አዋቂ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (አዋቂ ፡ ነው) አዋቂ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ አዋቂ ፡ ነው (አዋቂ ፡ ነው) ሁሉን ፡ ደርሶ ፡ ውብ ፡ ሊያደርገው ፡ ጌት ፡ በጊዜው ማጉረምረሜ ፡ ለምንድንነው ፡ እስኪ ፡ ላምልከው ትላንትና ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ማኅተሙም ፡ ያኔ ፡ ፈታህ ፡ ዛሬም ፡ እልሻዳይ ፡ ነው ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (ኤሻዳይ ፡ ነው) (፪x) ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው (ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው) (፪x) ኤልሻዳዬ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) አዶናዬ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)