Loading
Singer
ሳይሳሱ ፡ ፍቅሩን ፡ ወግተው ፡ ውርደት ፡ አለበሱት ስለፈወሳት ፡ ብለው ፡ ባፈቀረ ፡ ጠሉት የደሃ ፡ አዛኝ ፡ የሆንከው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ይገባ ፡ ነበረ ፡ ወይ ፡ ለእኔ ፡ ያፈጉት ፡ ነፍስ አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x) አንተ ፡ ፍቅር ፡ ነህና ፡ ልትጠላኝ ፡ አቃተህ ነፍሴን ፡ ከእሳት ፡ አወጣህ ፡ እራስህን ፡ ጐድተህ የእኔ ፡ የሆነ ፡ ምን ፡ አለኝ ፡ እራሴም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ደጋግመህ ፡ አድምጠኝ አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x) ኑሮዬና ፡ ተግባሬ ፡ ለእኔ ፡ ባይጥመኝም ጠላቴ ፡ የወጋኝ ፡ ቢያደናቅፈኝም አንድ ፡ ጊዜ ፡ ቆርጬ ፡ ተከትዬሃለሁ ድካም ፡ እንኳን ፡ ቢያጠቃኝ ፡ እከተልሃለሁ አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x) ያ ፡ የምድር ፡ ጨለማ ፡ አይሎ ፡ እንዳይውጠኝ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ጌታዬ ፡ ሳጠፋ ፡ ገስጸኝ መንበርከክን ፡ ይወዳል ፡ ሥጋ ፡ ለዓለም ፡ ነገር ጽናትህን ፡ እሻለሁ ፡ ከቶ ፡ እንዳልቀየር አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንከው ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስከው ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስቲ ፡ ና የማዋይህ ፡ አለኝና (፪x)