Loading
Singer
አይቋረጥም ፡ ከጀመርኩት ፡ ምሥጋናዬ እጨምራለሁ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታዬ ይገባዋልና (፫x) አይቋረጥም ፡ ከጀመርኩት ፡ ምሥጋናዬ እጨምራለሁ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታዬ ይገባዋልና (፫x) እስቲ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ያለው (፬x) ኢየሱስ ፡ በሕይወቱ ፡ የሆነው ፡ ብቸኛ አመልካለሁ ፡ የሚል ፡ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስርአት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ (፪x) አሃሃሃ ፡ እስቲ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ የተደረገለት አሃሃሃ ፡ ድቅድቅ ፡ ጨለማው ፡ የተገፈፈለት አሃሃሃ ፡ እድፋሙ ፡ ልብሱ ፡ የተቀየረለት አሃሃሃ ፡ ሃማ ፡ እያየ ፡ የተፈረደለት አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስራት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ እኔ ፡ አለበኝ ፡ ውለታው ፡ እኔ ፡ አለብኝ እኔ ፡ አለብኝ ፡ ውለታው ፡ ዝምበል ፡ አትበሉኝ (፪x) አሃሃሃ ፡ እስቲ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ፀሐይ ፡ የወጣለት አሃሃሃ ፡ የተማሰ ፡ ጉድጓድ ፡ የተደፈነለት አሃሃሃ ፡ ሟርቱ ፡ ድግምቱ ፡ የተረገጠለት አሃሃሃ ፡ ብርቱ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተሟገተለት አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስራት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ አሃሃሃ ፡ እስቲ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ውለታ ፡ ያለበት አሃሃሃ ፡ ሰባራ ፡ ልቡ ፡ የተጠገነለት አሃሃሃ ፡ ሞቱ ፡ ሲታወጅ ፡ ትንሳኤ ፡ የሆነለት አሃሃሃ ፡ ጌታ ፡ ነገሩን ፡ የገለበጠለት አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስራት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ አይቋረጥም ፡ ከጀመርኩት ፡ ምሥጋናዬ እጨምራለሁ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታዬ ይገባዋልና ፡ ይገባዋልና እስቲ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ያለው (፬x) ኢየሱስ ፡ በሕይወቱ ፡ የሆነው ፡ ብቸኛ አመልካለሁ ፡ የሚል ፡ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ