Loading
Singer
አንተ ፡ ላወቁብህ ፡ ክብር ፡ ነህ የማዕረግ ፡ መጐናፀፊያ የሃዘኑ ፡ ዘመን ፡ ማስረሻ ከማይነጥፍ ፡ ሰላም ፡ መድረሻ በዕረፍት ፡ ወንዝ ፡ ዳር ፡ ይተከላል ያገኘህ ፡ ከምንጭ ፡ ዳር ፡ ይኖራል ዕርዳታው ፡ ከሰማይ ፡ ደጅ ይወርዳል ፡ የእግዚአብሔር/የአምላኩ ፡ እጅ (፪x) አዝ፦ እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ (፪x) በሰማይ ፡ በምድር ፡ ማይገኝ ቢተካስ ፡ በሌላ ፡ ማያሰኝ መኖሪያህ ፡ በብርሃናት ፡ ውስጥ ውበት ፡ ነህ ፡ ለርስትህ ፡ ጌጥ ለዘለዓለም ፡ ትኖራለህ ማያረጁ ፡ ዓመታት ፡ ይዘህ ለሁሌ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ/የእኔ ፡ ምርጫ ከአዕላፋት ፡ አግኝተህ ፡ ብልጫ (፪x) አዝ፦ እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ (፪x) ለሰማይ ፡ ዉበትን ፡ የሰጠህ ለምድር ፡ ዳርቻን ፡ ያበጀህ እኔን ፡ በአምሳልህ ፡ መፍጠርህ የከበርሁ ፡ አርገህ ፡ ማየትህ ልቤ ፡ በመደነቅ ፡ ተሞላ ክብሬ ፡ ሊያዜምልህ ፡ ተነሳ ከልብ ፡ የሚፈልቅ ፡ ምሥጋና መስዋዕቴ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይግባ (፪x) አዝ፦ እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ (፪x)