Loading
Singer
ሳሙኤልም ፡ ወደ ፡ ሳኦል ፡ መጣ ሳኦልም ፡ አንተ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የተባረክ ፡ ሁን የእግዚአብሔርን ፡ ትዕዛዝ ፡ ፈጽሜአለሁ ፡ አለው ሳሙኤልም ፡ ይህ ፡ በጆሮዬ ፡ የምሰማው ፡ የበጐች ፡ ጩኸትና የበሬዎች ፡ ግሳት ፡ ምንድን ፡ ነው? አለ ሳኦልም ፡ ህዝቡ ፡ ለአምላክህ ፡ ይሰውአቸው ፡ ዘንድ መልካሞቹን ፡ በጐችና ፡ በሬዎችን ፡ አድነዋቸዋልና አማሌቃዊያንም ፡ አምጥተዋቸዋል የቀሩትንም ፡ ፈጽመን ፡ አጠፋን ፡ አለው ሳሙኤልም ፡ ለሳኦል ፡ አለቀሰ እግዚአብሔርም ፡ በእስራኤል ፡ ላይ ፡ ሳኦልን ፡ ስላነገሠ ፡ ተጸጸተ እስከመቸ ፡ ድረስ ፡ ለሳኦል ፡ ታለቅሳለህ ውረድ ፡ ቤተልሔም ፡ በቀንድ ፡ ዘይት ፡ ሞልተህ ከልጆቹ ፡ መሃል ፡ አዘጋጅቻለሁ ወደ ፡ እሰይ ፡ ቤት ፡ ግባ ፡ ንጉስ: እቀባለሁ ሲለኝ ፡ አግዚአብሄር ፡ ፈራሁ ፡ ተደናገጥሁ ሳኦል ፡ እንዳይሰማ ፡ ብዬ ፡ እጅጉን ፡ ፈራሁ አንዲት ፡ ጊደር ፡ ይዤ ፡ ጌታዬ ፡ እንዳዘዘኝ ጠራሁት ፡ እሰይን ፡ ልጆቹን ፡ እንዲያሳየኝ በእውነት ፡ መልኩ ፡ ያማረ ፡ ቁመናው ፡ ሸበላ ወደእኔ ፡ የተጠጋ ፡ ኤልያብ ፡ ነው ፡ ለካ እግዚአብሔር ፡ ሚቀባው ፡ በፊቴ ፡ ይህ ፡ አለ ለእስራኤል ፡ ንጉሥ ፡ ኧረ ፡ እፎይ ፡ ተገኘ ብዬ ፡ በውስጤ ፡ አስቤ ፡ ልቀባው ፡ ስጠጋ እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ፡ አትቸኩል ፡ በል ፡ ረጋ ሰው ፡ ፊትን ፡ እንደሚያይ ፡ እኔ ፡ አላይምና በዓይኔ ፡ ፊት ፡ ቀሏል ፡ አልያብን ፡ አትቀባ (፪x) ሌሎችም ፡ ሰባቱ ፡ አለፉ ፡ በፊቴ እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ፡ አልመረጥኩም ፡ እኔ ልጆቹም ፡ አለቁ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ የቀረው የሚቀባው ፡ የታል: ሰዉን: ግራ ፡ ገባው የቀረ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ እነዚሁ ፡ ናቸው እስኪ ፡ እሰይ ፡ ልጆችህን ፡ በደንህ ፡ ቁጠራቸው ገና ፡ ታናሽ ፡ አለ ፡ በጐች ፡ የጠብቃል አለኝ ፡ መለሰና ፡ ሥሙ ፡ ዳዊት ፡ ይባላል (፪x) ተጠርቶ ፡ መጣና ፡ በእኔ ፡ ፊት ፡ ቆመ እግዚአብሔርም ፡ አየው ፡ ዓለኝ ፡ ቀባው ፡ ሂደህ የአምላኬ ፡ መንፈስ ፡ ወደደው ፡ አረፈበት ዳዊት ፡ ያ ፡ እረኛው ፡ በእውነት ፡ አማረበት እግዚአብሔር ፡ ለካስ ፡ መቼ ፡ ፊትን ፡ ያያል ልቡን ፡ ከወደደ ፡ እረኛን ፡ ይቀባል እኔም ፡ ታሪክ ፡ አለኝ ፡ የዳዊትን ፡ መሳይ አምላኬ ፡ ከትቢያ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ ሲያነሳኝ እግዚአብሔር ፡ ለካስ ፡ መቼ ፡ ፊትን ፡ ያያል ልቡን ፡ ከወደደ ፡ ምስኪኑን ፡ ያከብራል እኔም ፡ ታረክ ፡ አለኝ ፡ የዳዊትን ፡ መሳይ አምላኬ ፡ ከትቢያ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ ሲያነሳኝ በሰው ፡ ዓይን ፡ ሲታዩ ፡ ዓይን ፡ የሚሞሉ ትከሻቸው ፡ ሰፊ ፡ ቁመናቸው ፡ ብቁ አልጠፉም ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ አገሩን ፡ ሞልተዋል በጊዜ ፡ . (3) . እንጂ ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ ከብረዋል ለምን ፡ እንደወደደኝ ፡ በውል ፡ ባይገባኝም ስለእራሴ ፡ ማውቀው ፡ ውብ ፡ ታሪክ ፡ የለኝም እንደ ፡ እስራኤል ፡ በዕፍረት፡ ነበርኩ ፡ እራቁቴን ኢየሱሴ ፡ መጥቶ ፡ ጠጋ ፡ ባያለብሰኝ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ለካስ ፡ መቼ ፡ ፊትን ፡ ያያል ልቡን ፡ ከወደደ ፡ እረኛን ፡ ይቀባል እኔም ፡ ታረክ ፡ አለኝ ፡ የዳዊትን ፡ መሳይ አምላኬ ፡ ከትቢያ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ ሲያነሳኝ