Loading
Singer
ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x) እናት ፡ እንኳን ፡ ልጇን ፡ ትረሳ ፡ ይሆናል ጓደኛም ፡ ወዳጅም ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ይከዳል አንተ ፡ ግን ፡ አትከዳም ፡ ለዘለዓለም ፡ ነህ ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ለእኔ ፡ እጅግ ፡ ቅርብ ፡ ነህ ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x) ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ለራስህ ፡ የለየኸኝ ከፊት ፡ እየቀደምክ ፡ እኔን ፡ የመራኸኝ እጆቼን ፡ እየያዝክ ፡ ክፉን ፡ ያሳለፍከኝ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ በእውነት ፡ የወደድከኝ ፍቅር ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ወዳጅ ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው አባት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ረዳት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የቅርብ ፡ ወዳጄ አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይምሮ ፡ መቼ ፡ እኖራለሁ ግን ፡ አንተ ፡ ይዘኸኝ ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ ለነገም ፡ አልፈራም ፡ በእጁ ፡ ውስጥ ፡ ነኝ አመልካለሁ ፡ አንተን ፡ አባት ፡ ስለሆንከኝ ፍቅር ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ወዳጅ ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው አባት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ረዳት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የቅርብ ፡ ወዳጄ አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x) ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x)