Loading
Singer
እንዳለፈ ፡ ውኃ ፡ መከራዬን ፡ አስረሳኝ (፪x) እንደ ፡ ጠዋት ፡ ፀሐይ ፡ ሕይወቴን ፡ አበራው (፪x) እንደ ፡ ቀትር ፡ ደግሞ ፡ አደመቀው ፡ እንደገና (፪x) ኧረ ፡ እንደው (፪x) ፡ ምን ፡ ይሻለኛል ዝም ፡ ብሎ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባርከኛል ፣ ይባርከኛል (፪x) ኧረ ፡ በረከቱ ፡ ገደብ ፡ አጣ (፬x) አዎ ፡ ለማዕበሉ ፡ ገደብ ፡ አለው ለወጀቡ ፡ ገደብ ፡ አለው ለመከራው ፡ ገደብ ፡ አለው ግን ፡ ለበረከቱ ፡ ገደብ ፡ የለው (፬x) እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳመልክህ እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳከብርህ እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ስወድህ እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ስሰጥህ የሰማያትንም ፡ መስኮቶች ፡ ከፈትክና (፫x) በረከትን ፡ አወረድከው ፡ እንደገና (፫x) እንደገና (፬x) ኧረ ፡ በረከቱ ፡ ገደብ ፡ አጣ (፬x) እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላሳያችሁ ድንቅ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አምላካችሁ (፫x) እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሞላው በመስፈሪያው ፡ ሰፈረው ነቀነቀውና ፡ ጨቆነው (፬x) ይባርካል ፡ እጁ ፡ ያጠግባል የልብንም ፡ መሻት ፡ ሁሉ ፡ ይሰጣል የላይኛውን ፡ እና ፡ የታችኛውን ፡ ምንጪ ሌላ ፡ ማን ፡ ይሰጣል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እንጂ (፪x) አዎ ፡ ለሀዘኑ ፡ ገደብ ፡ አለው ለለቅሶውም ፡ ገደብ ፡ አለው ለጭንቀቱም ፡ ገደብ ፡ አለው ለእንቆቅልሽ ፡ ገደብ ፡ አለው ለችግሩ ፡ ገደብ ፡ አለው ለማጣቱ ፡ ገደብ ፡ አለው ለበሽታው ፡ ገደብ ፡ አለው ግን ፡ ለበረከቱ ፡ ገደብ ፡ የለው (፮x) ኧረ ፡ በረከቱ ፡ ገደብ ፡ አጣ (፮x)