Loading
Singer
ማህጸኗ ፡ ቢደርቅ ፡ . (1) . ፡ ይዟት ተስፋዋ ፡ ተሟጦ ፡ ልጅ ፡ መውለድ ፡ ቢያቅታት የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ መቼ ፡ አረጀና ይወለዳል ፡ ይስሃቅ ፡ እርሱ ፡ ብሏልና (፪x) አዝ፦ ኧረ ፡ አመስግኑልኝ ፡ ይህን ፡ ጀግና ፡ ጌታ ከፍ ፡ ይበል ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ በዕልልታ እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን (፪x) አብርሃም ፡ ቢያረጀም ፡ ሳራም ፡ ብትደካክም ሁኔታውን ፡ አይተው ፡ የማይሆን ፡ ቢመስልም ለጌታ ፡ ምን ፡ አቅቶት ፡ ምን ፡ ተስኖት ፡ ያውቃል ይስሃቅን ፡ ሰጥቷቸው ፡ አስደንቋቸዋል (፪x) አዝ፦ ኧረ ፡ አመስግኑልኝ ፡ ይህን ፡ ጀግና ፡ ጌታ ከፍ ፡ ይበል ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ በዕልልታ እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን (፪x) የሚያስፈልግህን ፡ በጊዜው ፡ ያደርጋል ታምነህ ፡ ከተቀመጥክ ፡ ቃሉንም ፡ ያከብራል አድራሻህን ፡ አድርገው ፡ ከዙፋኑ ፡ ሥር ፈጥኖ ፡ ይረዳሃል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር አድራሻሽን ፡ አድርጊው ፡ ከዙፋኑ ፡ ሥር ፈጥኖ ፡ ይረዳሻል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር አዝ፦ ኧረ ፡ አመስግኑልኝ ፡ ይህን ፡ ጀግና ፡ ጌታ ከፍ ፡ ይበል ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ በዕልልታ እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን እርሱ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛስ ፡ አምላካችን ሲሰራ ፡ ስላየን ፡ ዛሬም ፡ በሕይወታችን (፪x)