Loading
Singer
አዝ፦ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በምክሩ ፡ ድግፍ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በቃሉ ፡ ድግፍ አርጐ ፡ የሚመራ ፡ በዘመናት ፡ መሃል እየሰባበረ ፡ ቅጥሩን ፡ የሚያዘልል ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እህ (፪x) የአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ምክሩ : ሳይለየኝ ፡ ማስተማሩ ልክ ፡ እንደ ፡ ዓይን ፡ ብሌን : ተንከባክቧት ፡ ሕይወቴን (፪x) እንዳልወድቅ ፡ እንዳልጠፋ : እየሰጠኝ ፡ ተስፋ ይኸው ፡ አለሁኝ ፡ በቤቱ : እየዘመርኩ ፡ ምህረቱን (፪x) አዝ፦ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በምክሩ ፡ ድግፍ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በቃሉ ፡ ድግፍ አርጐ ፡ የሚመራ ፡ በዘመናት ፡ መሃል እየሰባበረ ፡ ቅጥሩን ፡ የሚያዘልል ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እህ (፪x) በጉያዎቹ ፡ ሸሽጐ : ከመከራው ፡ ቀን ፡ ታድጐ ጠላቶቼ ፡ እንደጥላ : ቀሩና ፡ ወደ ፡ ኋላ (፪x) ያንን ፡ ዘመን ፡ በእርሱ ፡ አልፌ : ከሞት ፡ ወጥመድ ፡ ተርፌ ከክብር ፡ ጋር ፡ ዛሬን ፡ እንዳይ : ፈቀደልኝ ፡ ከሰማይ (፪x) አዝ፦ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በምክሩ ፡ ድግፍ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በቃሉ ፡ ድግፍ አርጐ ፡ የሚመራ ፡ በዘመናት ፡ መሃል እየሰባበረ ፡ ቅጥሩን ፡ የሚያዘልል ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እህ (፪x) በሃሩሩ ፡ በበረሃ : አፍለቅልቆ ፡ ከአለት ፡ ውኃ የመላእክትን ፡ መና : ከሰማይ ፡ ያወርድና (፪x) በእሳት ፡ አምድ ፡ በደመና : ከፊት ፡ ፊት ፡ ይመራና ወደ ፡ ተስፋይቱ ፡ ምድር : ያደርሰኛል ፡ በክብር (፪x)