Loading
Singer
Updated 10/5/2026
በስመአብ ፡ ወወልድ ፡ ወመፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንድ ፡ አምላክ ይሄ ፡ ጋብቻ ፡ የተባረከ ፡ ጋብቻ ፡ ይሁንልን ፡ አሜን አዝ፦ አዲስ ፡ ኑሮ ፡ አዲስ ፡ ቤት ፡ አሃዱ ፡ የተባለው ፡ ዛሬ በመልካም ፡ እንዲዘልቅ ፡ ይህ ፡ የፍቅር ፡ ጅማሬ እንመርቃቹሃለን ፡ አሜን (፮x) በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ተባረኩ ፡ ብለን ፡ እንመርቃቹሃለን (፪x) ክርስቶስ ፡ እርሱ ፡ የሆነው ፡ መሰረት እራስ ፡ ሆኖ ፡ ይንገሥበት ፡ እዚህ ፡ ይግባልን??? ፡ ቸርነት ትዳሩም ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተመርቶ የባርኮት ፡ ሽታ ፡ ሸቶ ፡ በምሳሌነት ፡ ተሞልቶ ከድግስ ፡ ያለፈ (አዎ) ፡ በሕይወታቸው ፡ ጉዞ (አዎ) ይምራቹህ ፡ እጃችሁን ፡ ይዞ አዝ፦ አዲስ ፡ ኑሮ ፡ አዲስ ፡ ቤት ፡ አሃዱ ፡ የተባለው ፡ ዛሬ በመልካም ፡ እንዲዘልቅ ፡ ይህ ፡ የፍቅር ፡ ጅማሬ እንመርቃቹሃለን ፡ አሜን (፮x) በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ተባረኩ ፡ ብለን ፡ እንመርቃቹሃለን (፪x) ቤተሰብ ፡ ጤናማ ፡ ቤተክርስቲያን ያድርጋት ፡ እንደብርሃን ፡ በፀጋው ፡ ብዛት ፡ ለማዳን የደስታ ፡ ምንጭ ፡ ሆኖ ፡ ይፍለቅለቅበት የተጠሙም ፡ የሚረኩበት ፡ ያዘኑም ፡ የሚደሰቱበት እግዚአብሔር ፡ አዘዘ (አዎ) ፡ ጋብቻ ፡ እንዲከበር (አዎ) ከጥንቱም ፡ ልክ ፡ እንደዚህ ፡ ነበር ቃልኪዳን ፡ አላቹህና ፡ ከእግዚአብሔር ብዙ ፡ ተባዙ ፡ ተባልን ፡ የአምላካቹህ ፡ ባርኮት ፡ ነው ውለዱ ፡ ክበዱ ፡ ይሁን ፡ ደስታ በፍቅር ፡ አምላክ ፡ በጌታ ፡ በሕይወታችሁ ፡ አለኝታ እግዚአብሔር ፡ ያኖራል (አዎ) ፡ መኖሪያቹህ ፡ ሆኖ (አዎ) ማን ፡ አፍሯል ፡ በእርሱ ፡ ተማምኖ አዝ፦ አዲስ ፡ ኑሮ ፡ አዲስ ፡ ቤት ፡ አሃዱ ፡ የተባለው ፡ ዛሬ በመልካም ፡ እንዲዘልቅ ፡ ይህ ፡ የፍቅር ፡ ጅማሬ እንመርቃቹሃለን ፡ አሜን (፮x) በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ተባረኩ ፡ ብለን ፡ እንመርቃቹሃለን (፪x)