Loading
Singer
በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ ለፍቻለሁ በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ እሮጫለሁ (፪x) ያላንተማ ፡ ደስ ፡ ብሎት ፡ ተድላን ፡ የቀመሰ ፡ እንደሌለ በጐ ፡ ስጦታ ፡ ፍፁም ፡ በረከት ፡ ከላይ ፡ እንደሆነ (፪x) የገባኝ ፡ ያው ፡ ብዙ ፡ ለፍቻለሁ ዛሬ ፡ ግን ፡ በቃ ፡ አቅም ፡ አጥቻለሁ ያስጨነቀኝ ፡ የረበሸኝ ፡ የዛሬውን ፡ ነገሬ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ሰጠሁህ ፡ ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ዘመኔን እንካ ፡ ዘላለሜን ፡ እንካ (እንካ) እንካ ፡ ዘላለሜን ፡ እንካ (፪x) እንካ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ዘል-ዘለዓለሜን (ዘላለሜን) ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ኑሮዬን በቃ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ዘል-ዘለዓለሜን (በቃ) ጌታ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ዘመኔን በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ ለፍቻለሁ በራሴማ ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ እሮጫለሁ (፪x) በከንቱ ፡ ይደክማል ፡ ቤተ ፡ ሰሪ በከንቱ ፡ ቅጥር ፡ ጠባቂ በሌለህበት ፡ ከንቱ ፡ ሩጫ መውደቅ ፡ መላላጥ ፡ መታመም ፡ ብቻ (፪x) የገባኝ ፡ ያው ፡ ብዙ ፡ ለፍቻለሁ ዛሬ ፡ ግን ፡ በቃ ፡ አቅም ፡ አጥቻለሁ ያስጨነቀኝ ፡ የረበሸኝ ፡ የዛሬውን ፡ ነገሬ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ሰጠሁህ ፡ ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ዘመኔን እንካ ፡ ዘላለሜን ፡ እንካ (፬x) እንካ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ዘለዓለሜን ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ይኸው ፡ ዘመኔን በቃ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ እንካ ፡ ዘላለሜን (በቃ) ጌታ ፡ ሰጥቻለሁ ፡ ውሰድ ፡ ዘመኔን