Loading
Singer
አንደበቴ ፡ አይፈታም ፡ ሥራ ለምሥጋና ፡ ስለ ፡ ተሰራ የልቤ ፡ ሀሳብ ፡ የአፌ ፡ ቃል አማረልኝ ፡ ዕልልታ ፡ ይዟል አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x) ሁሉም ፡ ነገር ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው የሚታየው ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው የሚሰማው ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው ክብር ፡ ዝና ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው አሃ ፡ አሃ ፡ አንተን ፡ ፈልጌ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ውስጤማ ፡ ናፍቆ አሃ ፡ አሃ ፡ ፍቅርህ ፡ ገባብኝ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ በልቤ ፡ ዘልቆ አሃ ፡ አሃ ፡ ይኸው ፡ ሽብሸባ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ለስምህ ፡ ጉዳይ አሃ ፡ አሃ ፡ የእኔስ ፡ እልልታ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ይሂድ ፡ ወደላይ አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x) አንተ ፡ በሰራኸው ፡ አልወስድም ፡ ምሥጋና ልቤን ፡ ከፈትኩ ፡ እንጂ ፡ ምን ፡ አደረኩና አንተ ፡ በሰራኸው ፡ አልወስድም ፡ ምሥጋና እንኳን ፡ ተቀንሶ ፡ መቼ ፡ ይበቃና ይኸው (፪x) ፡ ዕልልታው ፡ ይኸው (፪x) ይኸው (፪x) ፡ ሽብሸባው ፡ ይኸው (፪x) ይኸው (፪x) ፡ እልልታው ፡ ይኸው (፪x) ይኸው (፪x) ፡ አምልኮው ፡ ይኸው (፪x) ባለቤቱ ፡ የምሥጋና ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አለና ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይኸውልህ ፡ ይኸው ፡ ጌታ ባለቤቱ ፡ የምሥጋና ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አለና ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይገባሀል ፡ የእኔ ፡ ጌታ መሻቴ ፡ የእኔማ ፡ ደስታ ፡ የአምልኮ ፡ ሽታ አላማ ፡ የመፈጠሬ ፡ ለዚህ ፡ ነው ፡ ላምልክ ፡ አብሬ ቅሬታ ፡ የለም ፡ ትካዜ ፡ ምስጋናን ፡ ባሰብኩኝ ፡ ጊዜ አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x) አንደበቴ ፡ አይፈታም ፡ ሥራ ለምሥጋና ፡ ስለ ፡ ተሰራ የልቤ ፡ ሀሳብ ፡ የአፌ ፡ ቃል አማረልኝ ፡ ዕልልታ ፡ ይዟል አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x) ሁሉም ፡ ነገር ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው ገንዘብ ፡ ንብረት ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው ስልጣን ፡ ሹመት ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው ዘውዱ ፡ ንግሱ ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x) ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይኸውልህ ፡ ይኸው ፡ ጌታ ባለቤቱ ፡ የምሥጋና ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አለና ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይገባሀል ፡ የእኔ ፡ ጌታ