Loading
Singer
እኔን ፡ ለክብር ፡ ለሽልማት ፡ ያበቃኝ እግዚአብሔር ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ አነሳኝ (፪x) በሰው ፡ ዓይንም ፡ አልሞላ ነኝ ፡ እኮ ፡ ደካማ ግን ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ ፡ የተወደድኩኝ በእግዚአብሔር ፡ የተመረጥኩኝ (፪x) ከሰው ፡ ተራ ፡ የሚያድን ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ የለኝ ጐሽ ፡ የእኔ ፡ ልጅ ፡ ተብሎ ፡ የሚያስመሰግን ምህረትህና ፡ ፍቅርህ ፡ ሰው ፡ አድርገውኛል ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ ያዘምሩኛል አዝ፦ ተሰጥቼ ፡ ፊትህ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ባመልክህ ያንስብሃል ፡ ለውለታህ ፡ ሲታሰብ (፪x) እርቃንህን ፡ አደባባይ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ ምንም ፡ ሳታጠፋ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተገፋህ ያ ፡ ሁሉ ፡ ልፋትህ ፡ እኔን ፡ ለማዳን ፡ ነው ከክብርህ ፡ ወርደህ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያልከው አዝ፦ ተሰጥቼ ፡ ፊትህ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ባመልክህ ያንስብሃል ፡ ለውለታህ ፡ ሲታሰብ (፪x) እኔን ፡ ለክብር ፡ ለሽልማት ፡ ያበቃኝ እግዚአብሔር ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ አነሳኝ (፪x) በሰው ፡ ዓይንም ፡ አልሞላ ነኝ ፡ እኮ ፡ ደካማ ግን ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ ፡ የተወደድኩኝ በእግዚአብሔር ፡ የተመረጥኩኝ (፪x) ሰው ፡ ሰውን ፡ የሚወደው ፡ በእራሱ ፡ ምርጫ ፡ ነው ድካም ፡ ያለበትን ፡ ማነው ፡ የሚቀበለው አንተ ፡ ግን ፡ ስትወደኝ ፡ ስትቀበለኝ ደካማ ፡ ነሽ ፡ ብለህ ፡ ፊትህን ፡ አልነሳኸኝ አዝ፦ ተሰጥቼ ፡ ፊትህ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ባመልክህ ያንስብሃል ፡ ለውለታህ ፡ ሲታሰብ (፪x)