Loading
Singer
ቃልህን ፡ ለማንበብ ፡ ዓይኔ ፡ ታወረ እንዳልጸልይ ፡ ጉልበቴ ፡ ታሰረ አንተን ፡ እንዳላስብ ፡ አዕምሮዬ ፡ ዛለ እግሬም ፡ ወደ ፡ ጥፋት ፡ ኮበለለ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል ወድቄያለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ ጠፋሁኝ ፡ ጌታ ፡ ካልደረስክልኝ ዓለም ፡ እንደ ፡ ጐርፍ ፡ አነከባለለኝ ከኃጢአት ፡ ባሕር ፡ ልሰምጥ ፡ ነውና ጌታ ፡ ቆይ ፡ እባክህ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ መች ፡ ጨቀንክ ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ በልጅህ አውቃለሁኝና ፡ ጉድለቴን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አሁን ፡ ኃጢአቴን ፡ ማረኝ የምመራበትን ፡ ብርሃን ፡ ስጠኝ አየሁ ፡ ጌታዬን ፡ ወዲህ ፡ ስመጣ እኔንም ፡ ከጥፋት ፡ ሊያወጣ እጁን ፡ ላከልኝ ፡ ፍፁም ፡ አዳነኝ ከእንግዲህስ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፍፁም ፡ ቸል ፡ አልልም ፡ እርሱን ፡ ስከተል እኔኑን ፡ ለመውሰድ ፡ ስለሚያስብ መስቀሉ ፡ ለእኔ ፡ ቢከብደኝ ፡ እንኳን ፍፁም ፡ ለመሸከም ፡ አልቦዝንም