Loading
Singer
ነፍሴ ፡ የአምላክሽን ፡ ክብር ፡ እይ ፡ ታላቅነቱ ፡ ይግባሽ ጌታ ፡ መሆኑን ፡ ተረጂ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ይሁን ፡ ልብሽ ቸል ፡ አትበይ ፡ አትርሺ ፡ በዙፋኑ ፡ የተቀመጠውን እንደሚገባሽ ፡ አክብሪው ፡ ማራኪሽ ፡ እርሱ ፡ ይሁን እኔም ፡ ልወቅህ ፡ ዛሬ ፡ ልወቅህ ፡ እንደሚገባኝ በፊትህ ፡ ልስገድልህ ፡ ክብርህን ፡ ጌታ ፡ አሳየኝ ክብርህን ፡ አይቶ ፡ እንደነበረ ፡ የሚቀር ፡ ማን ፡ ነው ብርሃንህን ፡ አይቶ ፡ የማይሰግድልህስ ፡ ማን ፡ ነው ነፍሴ ፡ እርሱን ፡ ማየት ፡ ብትችይ ፡ ውበቱ ፡ ቢታይሽ ከሁሉ ፡ የሚበልጥ ፡ መሆኑ ፡ ከልብስ ፡ ቢረዳሽ ሰላምሽ ፡ ይበዛል ፡ ታርፊያልሽ ፡ ይቀራል ፡ ሁከትሽ አምላክ ፡ እንደ ፡ አምላክነቱ ፡ ቢረዳሽ ነፍሴ ፡ አምላክሽ ፡ ጠርቶሻል ፡ የልጁን ፡ ክብር ፡ እንድታይ በምድር ፡ ኑሮ ፡ በሚፈርስ ፡ በድንክዋን ፡ ተይ ፡ አትታለይ አምላክ ፡ ይረዳሻል ፡ መሻትሽ ፡ እሱን ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፈልጊው ፡ ተጠሚው ፡ ተራቢው ፡ ጌታሽን ነፍሴ ፡ የእምነትን ፡ ብልጭታ ፡ አንጸባርቆልሻል አምላክ ፡ እንድታውቂው ፡ እንድትቀርቢው ፡ ይሻል አንድ ፡ ልጁን ፡ ልኮ ፡ እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ መርጦሻል ነፍሴ ፡ እባክሽ ፡ ይግባሽ ፡ አክብሪው ፡ እርሱ ፡ ይበልጥብሻል እዚህ ፡ ያደረሰሽ ፡ በስጋው ፡ መቼ ፡ ይለይሻል ሃጢያተኛ ፡ ሳለሽ ፡ ሞቶልሽ ፡ በደሙ ፡ አጽድቆሻል ከመልእክት ፡ በላይ ፡ አክብሮሽ ፡ በቀኙ ፡ አስቀምጦሻል ነፍሴ ፡ እባክሽ ፡ ይግባሽ ፡ እርሱ ፡ አክብሮሻል