Loading
Singer
አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ በዛና ፡ እንቆቅልሼ ፡ ለብዙ ፡ ዘመን ፡ አልቅሼ አንድ ፡ ቀን ፡ ዝናህን ፡ ሰማሁ ፡ ልነግርህ ፡ ከሳባ ፡ መጣሁ ተቀመጥ ፡ በዙፋንህ ፡ የልቤን ፡ እንድነግርህ አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ በግመል ፡ ሽቱ ፡ ጭኛለሁ ወርቅና፡ ዕንቁም ፡ ይዣለሁ ደክሞኛል ፡ ጓዜ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አድምጠኝ ፡ ያኔ ፡ አርፋለሁ አገሬን ፡ በዚህ ፡ ወክዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ ልውደቅ ፡ ጌታዬ አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ ሠማይና ፡ ምድርን ፡ ፈጥረሃል ፡ በጥበብህ ፡ ሁሉን ፡ አድርገሃል ከዓይንህ ፡ የተሰወረ ፡ አሸንፎህስ ፡ የኖረ ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ነበር ፡ ፍታልኝ ፡ የእኔንም ፡ ነገር አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ ገና ፡ ጥንት ፡ ሳለሁ ፡ በአገሬ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ የሰማሁት ፡ ወሬ ማመን ፡ ግን ፡ አቅቶኝ ፡ ነበር ፡ ልክ ፡ የለው ፡ የዕውቀትህ ፡ ነገር ጥበብህ ፡ ከአእምሮ ፡ ያልፋል ፡ ከሰማሁት ፡ ዝናህ ፡ ይበልጣል አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ