Loading
Singer
የገባልኝን ፡ ቃል ፡ እስከሚፈፅመው እግዚአብሔር ፡ ይተጋል እኔም ፡ አምነዋለሁ (፬x) የገባልኝን ፡ ቃል ፡ እስከሚፈፅመው እግዚአብሔር ፡ ይተጋል እኔም ፡ አምነዋለሁ (፬x) ፍፁም ፡ የማይገባ ፡ የማይመስል ፡ ነገር እንደምን ፡ ይሆናል ፡ የተባለ ፡ ቢሆን የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ በቃሉ ፡ የታመነ እውን ፡ ያደርገዋል ፡ ተስፋ ፡ ከእርሱ ፡ ካለ ስለዚህ ፡ አምላኬን ፡ እጠብቃለሁኝ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ እኔም ፡ እስካየው (፪x) ቀናቶች ፡ ቢረዝሙ ፡ ችግሩም ፡ ቢበዛ እምነቴም ፡ ቢፈተን ፡ ጠላትም ፡ ቢነሳ ቃል ፡ ተናግሯልና ፡ ይሆናል ፡ አይቀርም ጌታዬ ፡ ሲከፍተው ፡ ማንም ፡ አይዘጋውም ስለዚህ ፡ አምላኬን ፡ እጠብቃለሁኝ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ እኔም ፡ እስካየው (፪x) ዓይኖቹ ፡ ያዩኛል ፡ ጆሮውም ፡ ይሰማኛል የልቤን ፡ ጥያቄ ፡ ጌታዬ ፡ ያውቀዋል መልስ ፡ እስከሚመጣ ፡ እስከሚጐበኘኝ አፅንቶ ፡ የሚያቆም ፡ የተስፋ ፡ ቃል ፡ አለኝ ስለዚህ ፡ አምላኬን ፡ እጠብቃለሁኝ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ እኔም ፡ እስካየው (፪x)