Loading
Singer
በዙሪያዬ ፡ ያለው ፡ ነገሬ ፡ ይህን ፡ ባይነግሬኝ ነገርሽ ፡ ሞተ ፡ ተቀበረ ፡ በቃ ፡ ብለኝ አዲስ ፡ ነገር ፡ ማድረግ ፡ ሁልጊዜ ፡ ልማድ ፡ ያለው ፡ ጌታ ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ይተጋል ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ከፍታ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ የማምነው ፡ ጨለማሽ ፡ ይበራል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x) እኔ ፡ የማምነው ፡ ተራራሽ ፡ ይናዳል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x) አላምንም ፡ ሁኔታን ፡ አላምንም ፡ ችግሬን እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይሰራል ፡ ነገሬን (፪x) እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይከፍታል ፡ መቃብሬን (፪x) ልቤን ፡ ልጣል ፡ እንጂ ፡ በሚያስጥለው ፡ ጌታ በእርሱ ፡ ተደግፌ ፡ ጉልበቴን ፡ ላበርታ ታምራት ፡ ያሳየኛል ፡ ጌታ (፬x) በደረቁ ፡ አጥንቶች ፡ ነፍስን ፡ መዝራት እንደ ፡ ሰው ፡ ሲታሰብ ፡ በምን ፡ ጉልበት እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ቀላል ፡ ነው እጁ ፡ ድንቅ ፡ ይሰራል ፡ ትልቅ ፡ ነው ልጅ ፡ መውለድ ፡ በዘጠና ፡ ዓመት ለሣራ ፡ ከባድ ፡ ነው ፡ ሲገመት ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ካለ ፡ ሆነ ፡ ነው ታምር ፡ የሚሰራ ፡ ጌታ ፡ ነው [1] እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ ያልታሰበ ፡ ነገር ፡ ያደርጋል ፡ በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ የማምነው ፡ ጨለማሽ ፡ ይበራል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x) እኔ ፡ የማምነው ፡ ተራራሽ ፡ ይናዳል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x) አላምንም ፡ ሁኔታን ፡ አላምንም ፡ ችግሬን እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይሰራል ፡ ነገሬን (፪x) እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይከፍታል ፡ መቃብሬን (፪x) ልቤን ፡ ልጣል ፡ እንጂ ፡ በሚያስጥለው ፡ ጌታ በእርሱ ፡ ተደግፌ ፡ ጉልበቴን ፡ ላበርታ ታምራት ፡ ያሳየኛል ፡ ጌታ (፬x)