Loading
Singer
የጽድቅን ፡ ጥሩር ፡ ለብሼ ገነትም ፡ ጋሻ ፡ አንስቼ በቃል ፡ እውነት ፡ ታጥቄ እቆማለሁ ፡ ፀንቼ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x) በፍጹም ፡ ልቤ ፡ እሰግዳለሁ ሃሳቤን ፡ አስገዛለሁ በፈቃዴ ፡ እሸነፋለሁ ጌታዬን ፡ አመልከዋለሁ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x) በጽኑ ፡ ምክሩ ፡ ታምኜ በቅን ፡ ስርዓቱ ፡ ሄጄ ቅዱስ ፡ ሥሙን ፡ አከብራለሁ አምላኬን ፡ አመልከዋለሁ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x) እግዚአብሔርን ፡ እባርካለሁ ምሥጋናውም ፡ ሁሉ ፡ በአፌ ፡ ነው በእርሱ ፡ ፍቅር ፡ አኖራዋለሁ ዘለዓለም ፡ አመልከዋለሁ አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፬x)