Loading
Singer
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ አመልክሃለሁ ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ባነሳህ ፡ እኔስ ፡ መች ፡ ጠግባለሁ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ መሪ የፍጥረታት ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነዋሪ አዝ፦ እኔ ፡ እገረማለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ እያየሁ እኔስ ፡ እደነቃለሁ (፫x) ፡ ማዳኑን ፡ እያየሁ ሃሌሉ ፡ ሃሌሉያ ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ሥምህን ፡ ላክብር ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ጌታዬን ፡ ላክብር በገናን ፡ ልደርድር ፡ በፊትህ ፡ ሥምህን ፡ ልቀድስ ጣቶቼን ፡ ዘመቻ ያስተማርካቸው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ በክብር ፡ ላይ ፡ ክብር ፡ ይጨመርልህ በሰማይ ፡ በምድር ፡ አንተን ፡ አጣ ፡ የሚመስልህ አዝ፦ እኔ ፡ እገረማለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ እያየሁ እኔስ ፡ እደነቃለሁ (፫x) ፡ ማዳኑን ፡ እያየሁ ሃሌሉ ፡ ሃሌሉ-ያ ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ሥምህን ፡ ላክብር ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ጌታዬን ፡ ላክብር በነጋ ፡ በጠባ ፡ ከውስጤ ፡ ምሥጋና ፡ ይፈልቃል ያረክልኝ ፡ ተነግሮ ፡ ተዘምሮ ፡ መች ፡ ያልቃል አንተ ፡ ነህ ፡ እንጂ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ የለኝ ከኃጢአት ፡ አጥበህ ፡ ቀድሰህ ፡ ሥም ፡ ያወጣህልኝ አዝ፦ እኔ ፡ እገረማለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ እያየሁ እኔስ ፡ እደነቃለሁ (፫x) ፡ ማዳኑን ፡ እያየሁ ሃሌሉ ፡ ሃሌሉ-ያ ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ሥምህን ፡ ላክብር ልዘምር ፡ ልዘምር ፡ ጌታዬን ፡ ላክብር