Loading
Singer
ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ የሕይወቴ ፡ ዋልታ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ የቤቴን ፡ ምሰሶ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ መውደድህ (፪x) ምኔን ፡ አይቶ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ተገኝቶብኝ ከሰዉ ፡ መሃል ፡ ዓይኑ ፡ ያረፈብኝ ለፍቅር ፡ ብሎ ፡ ያልሆነው ፡ የለም በባዶ ፡ የሚወድ ፡ እኔ ፡ አላየሁም እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ መውደድህ (፪x) እኔ ፡ አላየሁም ፡ ሞቶ ፡ ሚታደግ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ሕያው ፡ የሚያደር እኔ ፡ አላየሁም ፡ በነፍሱ ፡ ቤዛ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ሁሉን ፡ የገዛ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ዘሬም ፡ አልሰማ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ኧረ ፡ እንዳንተማ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ለሁሉ ፡ አሳቢ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ ሰፊ ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ የሕይወቴ ፡ ዋልታ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ የቤቴን ፡ ምሰሶ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፪x) የዛሬውን ፡ እንጂ ፡ የነገው ማን ፡ ያውቃል ፡ ምን ፡ እንደሚያረገው ትላንትን ፡ ሳስበው ፡ አመንኩት አሳልፌ ፡ በእጁ ፡ ሰጠሁት (፪x) ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ነፍሴን ፡ በምክርህ የምታረካ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ሚስጥረኛዬ ፡ የልቤ ፡ የምለው እኔን ፡ የሚያውቀኝ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፫x)