Loading
Singer
አፍቅሮኝ ፡ ፍቅርን ፡ አስተማረኝ የማረኝ ፡ ምህረት ፡ አድርጊ ፡ ያለኝ በጌታ ፡ ለካ ፡ ይህም ፡ ይቻላል ለአሳዳጅ ፡ ምህረት ፡ ይደረጋል ገዳዬን ፡ በእጅህ ፡ ላይ ፡ አግኝቶ መመለስ ፡ መንገድ ፡ አሳይቶ እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ ፍቅር ፡ ማለት ሁሉንም ፡ መቀበል ፡ በምህረት (፪x) ምህረት ፡ አግኝቼ ፡ ምህረት ፡ አሰጣለሁ ይቅር ፡ ተብዪ ፡ ይቅር ፡ እላለሁ (፪x) ህግ??? ፡ ሳናደርግ ፡ በመሃከላችን መስዋዕት ፡ ለማቅረብ ፡ ምነው ፡ ችኮላችን ይቅር ፡ መባባሉ ፡ ማንንስ ፡ ገደለ ተቆጥተን ፡ መሸ ፡ ዋል ፡ አደርም ፡ አለ እንታረቅ ፡ አሃሃሃ ፡ እንታረቅ እንታረቅ ፡ አሆሆሆ ፡ እንታረቅ (፪x) አሁን ፡ እንታረቅ ፡ እርስ ፡ በእርሳችን ሳንሰዋ ፡ በፊት ፡ መስ ፡ ዋዕታችንን በአምላካችን ፡ ፊት ፡ እስቲ ፡ እንተቃቀፍ የሰጠውንም ፡ ቃል ፡ ከቶ ፡ አንተላለፍ እንታረቅ ፡ አሃሃሃ ፡ እንታረቅ እንታረቅ ፡ አሆሆሆ ፡ እንታረቅ (፪x) ምህረት ፡ አግኝቼ ፡ ምህረት ፡ አሰጣለሁ ይቅር ፡ ተብዪ ፡ ይቅር ፡ እላለሁ (፪x) ታናሹን ፡ ከታላቁ ፡ እኩል በአንድነት ፡ ማቀፍ ፡ መጠየቅ በዳዩን ፡ መጠየቅ ፡ ይቅርታ ይሄ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ ፡ የጌታ ለአፍቃሪ ፡ ፍቅር ፡ መስጠትማ ያለ ፡ ነው ፡ በዓለም ፡ ከተማ ጨካኝ ፡ ነው ፡ የሚሉትን ፡ ክፉ ይቻላል ፡ በወንጌል/በጌታ ፡ ማቀፉ (፪x) ምህረት ፡ አግኝቼ ፡ ምህረት ፡ አሰጣለሁ ይቅር ፡ ተብዪ ፡ ይቅር ፡ እላለሁ (፪x) እንታረቅ ፡ አሃሃሃ ፡ እንታረቅ እንታረቅ ፡ አሆሆሆ ፡ እንታረቅ (፪x)