Loading
Singer
እንሂድ ፡ ሲሉኝ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቤት ደስ ፡ ካለኝ ፡ ሓሴት ፡ ካደረኩት ስሄድማ ፡ ስገባ ፡ በፊቱ ፡ ሲቀበለኝ ፡ በብዙ ፡ ምህረቱ ይጨምራል ፡ ይበዛል ፡ ደስታዬ ፡ በመንፈሱ ፡ ሲነካኝ ፡ ጌታዬ በረከቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከቅዱሳን ፡ ጋራ ደግነቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከወገኖች ፡ ጋራ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በቤትህ ፡ ሰላም ፡ አለ ያዘነውን ፡ የሚያጽናና ፡ እያባበለ (፪x) በዓለም ፡ ካለው ፡ የተለየ ፡ ሰላም ፡ ደስታ አግኝቻለሁ ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ እኔ ፡ ስመጣ (፪x) ወደ ፡ ቤትህ ፡ ልገስግስ ፡ በመንፈስህ ፡ እንድዳሰስ ወደ ፡ ፊትህ ፡ ልገስግስ ፡ በእጆችህ ፡ እንድዳሰስ ወደ ፡ ክብርህ ፡ ልገስግስ ፡ በውበትህ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ ወደ ፡ ፀጋህ ፡ ልገግስ ፡ በመንፈስ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ ሁል ፡ ጊዜ ፡ በፊትህ ፡ የሚቆሙ ጥበብህን ፡ ከአንደበትህ ፡ የሚሰሙ (፪x) ባሪያዎችህ ፡ ኧረ ፡ እንደምን ፡ የታደሉ በማደሪያህ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ሁሌ ፡ የሚሉ በቤትህ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ሁሉ ፡ ሚሉ ወደ ፡ ቤትህ ፡ ልገስግስ ፡ በመንፈስህ ፡ እንድዳሰስ ወደ ፡ ፊትህ ፡ ልገስግስ ፡ በእጆችህ ፡ እንድዳሰስ ወደ ፡ ክብርህ ፡ ልገስግስ ፡ በውበትህ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ ወደ ፡ ፀጋህ ፡ ልገግስ ፡ በመንፈስ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ ልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ጥላ ለዚህ ፡ ዓለም ፡ ሐሩር ፡ ከለላ መኖሪያ ፡ ነህ ፡ በኧረፍት አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የአንተ ፡ ቢት ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይኖራል ፡ ታምኖ ሳይሰጋ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ ብሎ በቤትህ ፡ በመቅደስህ ፡ ምትሸከም ፡ አንተ ፡ ነህ እንሂድ ፡ ሲሉኝ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቤት ደስ ፡ ካለኝ ፡ ሓሴት ፡ ካደረኩት ስሄድማ ፡ ስገባ ፡ በፊቱ ፡ ሲቀበለኝ ፡ በብዙ ፡ ምህረቱ ይጨምራል ፡ ይበዛል ፡ ደስታዬ ፡ በመንፈሱ ፡ ሲነካኝ ፡ ጌታዬ በረከቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከቅዱሳን ፡ ጋራ ደግነቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከወገኖች ፡ ጋራ