Loading
Singer
የምድረ ፡ በዳው ፡ ድምጽ ፡ የአዋጅ ፡ ነጋሪው ፡ ቃል መንገዱን ፡ ጥረጉ ፡ አስተካክሉ ፡ ይላል ክብሩ ፡ ይገለጣል ፡ ኮረብታው ፡ ዝቅ ፡ ይበል ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ያያል አዝ፦ እኔ ፡ ነኝ ፡ ተራራው ፡ ትልቁ ፡ እንቅፋት የሕዝብህ ፡ ጉስቁልና ፡ የድካሙ ፡ ምክንያት ኦ ፡ ምንኛ ፡ ይመራል ፡ የትዕቢቱ ፡ ፅዋ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ዝቅ ፡ አርገኝ ፡ ሳይገለኝ ፡ ፍሬዋ ጌታ ፡ ትዕቢተኛውን ፡ እጅግ ፡ ይቃወማል ለትሁታኑ ፡ ግን ፡ ፀጋውን ፡ ይሰጣል ለስም ፡ አገልጋይ ፡ ነኝ ፡ ፀጋ ፡ ግን ፡ ያንሰኛል የእኔ ፡ ዝና ፡ ወጥቶ ፡ የአንተ ፡ ተሰውሯል አዝ፦ እኔ ፡ ነኝ ፡ ተራራው ፡ ትልቁ ፡ እንቅፋት የሕዝብህ ፡ ጉስቁልና ፡ የድካሙ ፡ ምክንያት ኦ ፡ ምንኛ ፡ ይመራል ፡ የትዕቢቱ ፡ ፅዋ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ዝቅ ፡ አርገኝ ፡ ሳይገለኝ ፡ ፍሬዋ ኦ ፡ ምን ፡ ይሻለኛል ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና ሰዎች ፡ አንተን ፡ ሊያይ ፡ ከቶ ፡ አልቻሉምና የልቤን ፡ ኮረብታ ፡ ተራራውን ፡ ናደው ፍሬም ፡ እንዲመጣ ፡ ቅንጣቱን ፡ ግደለው አዝ፦ እኔ ፡ ነኝ ፡ ተራራው ፡ ትልቁ ፡ እንቅፋት የሕዝብህ ፡ ጉስቁልና ፡ የድካሙ ፡ ምክንያት ኦ ፡ ምንኛ ፡ ይመራል ፡ የትዕቢቱ ፡ ፅዋ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ዝቅ ፡ አርገኝ ፡ ሳይገለኝ ፡ ፍሬዋ