Loading
Singer
አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x) የሚያውቅህ ፡ ነው ፡ የሚያውቀው የአንተ ፡ ፍቅር ፡ የገባው እህል ፡ ውሃ ፡ ማያሰኘው ከአንተ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አያምረው (፪x) አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x) ያየሁትን ፡ አይቼ ፡ ነው እንዲህ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ ፡ ምዘምረው ሊካድ ፡ የማይቻል ፡ እውነትህ ማርኮ ፡ አስቀርቶኛል ፡ ያ ፡ ፍቅርህ (፪x) አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x) ዝም ፡ ማለት ፡ እንዴት ፡ ያስችለኛል የእግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ይለኛል ለቀየረው ፡ ለርሱ ፡ የኔን ፡ ሕይወት ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምነው ፡ በሆንኩለት (፪x) አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x)