Loading
ልባምን ፡ ሴት ፡ ማን ፡ ሊያገኛት ፡ ይችላል ከእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ካልሆነ ፡ ከየት ፡ ይገኛል ከዝርግፍ ፡ ጌጥ ፡ ይልቅ ፡ ውስጧ ፡ የበለጠ በፀጋው ፡ መንፈሷ ፡ ሁሉ ፡ ያጌጠ ወርቅ ፡ አያምራት ፡ እርሷ ፡ ራሷ ፡ ወርቅ ፡ ናት ለይሉኝታ ፡ ምታስመጣው ፡ ጥሎሽ ፡ የላት መልካም ፡ አእምሮ ፡ የበሰለ ፡ ባህሪ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ፈሪ አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት ከውጭ ፡ ውበት ፡ የውስጥ ፡ ውበቷ ፡ በልጧል አካሄዷ ፡ ንግግሯ ፡ ይገልጣል ማስተዋሏ ፡ ዕውቀቷ ፡ የበዛ ፡ ነው የማመዛዘን ፡ ችሎታ ፡ ሁሉ ፡ ያለው (በጣም) እንደ ፡ ሰነፍ ፡ ሴቶች ፡ አትናገርም በመከራም ፡ ውስጥ ፡ ተስፋን ፡ አትቆርጥም ከአጥንቱ ፡ ነው ፡ እርሷ ፡ የተሰራችው ለዚህ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ የቻለችው አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት የባሏም ፡ ልብ ፡ ይተማመንባታል እውነተኛው ፡ ፍቅር ፡ ይመግባታል ትገዛለች ፡ ለቃሉ ፡ ለሃሳቡ በግድ ፡ ሳይሆን ፡ አሸንፏት ፡ ፍቅሩ ተወስና ፡ እርሷ ፡ ለእርሱ ፡ ተሰጥታ በሌላ ፡ ወንድ ፡ ልቧም ፡ ሳያመነታ አንድ ፡ ለአንድ ፡ አይደለም ፡ የእርሷ ፡ ሂሳብ እንደቃሉ ፡ አንድ ፡ ናት ፡ ያለ ፡ ሃሳብ አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት ገና ፡ ሌሊት ፡ በማለዳ ፡ ተነስታ (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት) ምግብ ፡ ለቤቷ ፡ ሰዎች ፡ ሁሉ ፡ ሰርታ (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት) ወገቧን ፡ በመቀነቷ ፡ ታጥቃለች (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት) ስራዋን ፡ በጊዜው ፡ ትጨርሳለች (እንዲህ ፡ አይነቷ) እንድትለፋ ፡ አይደለም ፡ እርሱ ፡ ያገባት (እንዲህ ፡ አይነቷ) እረዳት ፡ ናት ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ የገባት (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት) ሰራተኛው ፡ አይደለችም ፡ ለቤቱ (እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት) ናት ፡ ለባሏ ፡ ድምቀቱ ፡ ውበቱ (እንዲህ ፡ አይነቷ) አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፫x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት ውበት ፡ ሃሰት ፡ ነው ፡ ደምግባትም (ከንቱ ፡ ነው) ውበት ፡ ሃሰት ፡ ነው ፡ ደምግባትም (ከንቱ) እግዚአብሔርን ፡ የምትፈራ ፡ ሴት ፡ እርሷ ፡ ትመሰገናለች (ትመሰገናለች) እግዚአብሔርን ፡ የምትፈራ ፡ ሴት ፡ እርሷ ፡ ትመሰገናለች (እርሷ) (፪x) እግዚአብሔርን ፡ የምትፈራ ፡ ሴት ፡ እርሷ ፡ ትመሰገናለች (፪x) አዝ፦ እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፬x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፬x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት እንዲህ ፡ አይነቷ ፡ ናት (፬x) ፡ እውነተኛ ፡ ረዳት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.