Loading
Singer
የእኔን ፡ ሰው ፡ መሆን ፡ የፍጥረቴን ፡ ሚስጥር የደመነፍስ:ኑሮን ፡ ጠፍቶ ፡ የሚተረትር የታረደለኝ ፡ በግ ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ ሕይወት ፣ ያለኝ ፡ ነኝ እኔም ፡ ዝቅ ፡ በዬ ፡ ልስገድለት ፡ ለእርሱ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ምሥጋና (፬x) ነው ፡ ያለኝ (፪x) ተከተይኝ ፡ አለኝ ፡ ትምክቴን ፡ አስጥሎ የዓለም ፡ አይደለሽም ፡ አንቺ ፡ የእኔ ፡ ነሽ ፡ በሎ አክብሮት ፡ አምልኮ ፡ ለሌላው ፡ ለመስጠት ጉልበቶቼ ፡ ታጥፈው ፡ ሊንቀጠቀጡለት እንዲህ ፡ አይደረግም (፪x) ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ማንንም ፡ አይመስልም (፪x) ያልሳሳ ፡ ገበታን ፡ ጌታዬ ፡ አዘጋጅቶ ከሕይወት ፡ ቃል ፡ ማዕድ ፡ መንፈሴን ፡ አርክቶ እንዳዜም ፡ ካበቃኝ ፡ በሕያዋን ፡ ምድር ልሰግድ ፡ ይገባኛል ፡ ከንጉሡ ፡ እግር ፡ ሥር ይገባኛል (፪x) አምላኬ ፡ እኮ ፡ እኔን ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ አርጐኛል (፪x) ከምድራዊው ፡ ኑሮ ፡ ያለፈ ፡ አለ ፡ ብሎ የሞተልኝ ፡ ጌታ ፡ የእኔን ፡ እዳ ፡ ከፍሎ ክርስቶስን ፡ ለበስኩ ፡ እንዴት ፡ አምሮብኛል ክብሬና ፡ ሞገሴን ፡ ማን ፡ ያወልቅብኛል እንዲህ ፡ አይደረግም (፪x) ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ማንንም ፡ አይመስልም (፪x) የእኔን ፡ ሰው ፡ መሆን ፡ የፍጥረቴን ፡ ሚስጥር የደመነፍስ:ኑሮን ፡ ጠፍቶ ፡ የሚተረትር የታረደለኝ ፡ በግ ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ ሕይወት ፣ ያለኝ ፡ ነኝ እኔም ፡ ዝቅ ፡ በዬ ፡ ልስገድለት ፡ ለእርሱ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ምሥጋና (፬x) ነው ፡ ያለኝ ዕልልታ (፬x) ነው ፡ ያለኝ (፪x)