Loading
Singer
አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x) ሥምህን ፡ እንደዋዛ ፡ ተሽክሜዋለሁ ክርስቲያን ፡ ተብዬም ፡ ይኸው ፡ እጠራለሁ ውስጤ ፡ ቢመረመር ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም የመንፈስ ፡ ፍሬ ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ የለም አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x) የለየልኝም ፡ ከሃዲ ፡ አልሆንኩኝም ክርስቲያንም ፡ ሆኜ ፡ አልበረታሁም እንዲያው ፡ ለብ ፡ ብዬ ፡ አስቸግሬያለሁኝ ዛሬስ ፡ በንስሃ ፡ ተደፍቻለሁኝ አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x) ለክርስቲያኖች ፡ ለአንተ ፡ ያለኝ ፡ ፍቅር ላገልግልህም ፡ ሥምህን ፡ ላስከብር የነበረኝ ፡ ፀሎት ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ ትጋቴ እፍገመገማለሁ ፡ ከድቶኛል ፡ ብርታቴ አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x) ሽቅብ ፡ እንደመውጣት ፡ ቁልቁለት ፡ ሄጃለሁ ወደ ፡ ሞትም ፡ ደጃፍ ፡ በጣም ፡ ቀርቤያለሁ አሁንም ፡ በቃልህ ፡ ተገስጫለሁኝ ዳግም ፡ አንሳኝ ፡ ብዬ ፡ ተማጽኛለሁኝ አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x)