Loading
Singer
Updated 10/4/2026
ተጨንቃ ፡ ለነበረች ፡ ነፍሴ ፡ ጨለማን ፡ አይሆንም ፡ ሲል አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ሽሮ ፡ መርዶዬን ፡ ሲከለክል ከፊቴ ፡ ቀድሞ ፡ ሲወጣ ፡ ተራራን ፡ ሲደለድል ሥራዬን ፡ ሰርቶ ፡ ሲጨርስ ፡ ችግሬን ፡ ሲጠቀልል መቃብሬን ፡ ሲከፍተው ፡ ታምር ፡ ሲሰራ ነፍሴን ፡ እጅግ ፡ ሲያስጨንቅ ፡ በእኔ ፡ ሲፈራ ታምራት ፡ ሲያስለምደኝ ፡ ሲያሳየኝ ፡ ኖሬ እንዴት ፡ እሸበራለሁ ፡ እፈራለሁ ፡ ዛሬ አዝ፦ እንዴት ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ (፫x) ለምን ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ (፫x) የተሸከመኝ ፡ ትልቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (፬x) ስንቱን ፡ ሸለቆ ፡ ስንቱን ፡ ተራራ ጥሼ ፡ ሄጃለሁ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ (፪x) እያሪኮዬ ፡ ቅጥሩ ፡ ሲፈርስ አይታለች ፡ ነፍሴ ፡ በኢየሱስ (፪x) ስለዚህ ፡ አልፈራም ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ ማይናወጥ (፪x) በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ ማይናወጥ (፪x) አዝ፦ እንዴት ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ (፫x) ለምን ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ (፫x) የተሸከመኝ ፡ ትልቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (፬x) በእሳት ፡ ማሃል ፡ መንገድ ፡ ያለው ፡ ጌታ መቼ ፡ ትቶኝ ፡ ያውቃል ፡ አንድ ፡ አፍታ ማዕበልና ፡ ወጀቡን ፡ አራምዶ ያሻግረኛል ፡ ከባህር ፡ ማዶ ስለዚህ ፡ አልፈራም ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ ማይናወጥ (፪x) በዙፋኑ ፡ እያለ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ የማይናወጥ (፪x) አዝ፦ እንዴት ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ (፫x) ለምን ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ (፫x) የተሸከመኝ ፡ ትልቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (፬x)