Loading
Singer
Updated 8/2/2026
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ይችላል እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ይችላላ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ይችላል እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ይችላላል ሃጥያትን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይቅር ፡ ይላል ከዓመጻም ፡ እርሱ ፡ ያነጻል ቁጣው ፡ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ነው ምህረቱ ፡ ግን ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው እርሱ ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ እርሱ ፡ ፈጥራል ለእግዚአብሔር ፡ የለም ፡ የሚሳነው ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ሁሉን ፡ ችይ ፡ ነው በኃይሉ ፡ ብዛትና ፡ በችሎቱ አንዳች ፡ የማይታጣው ፡ ነው ፡ ብርቱ እግዚአብሔር ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነው የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ ፡ ነው አይደክምም ፡ እርሱ ፡ አይታክትም ማስተዋሉም ፡ አይመረመርም እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፊተኛ ፡ ነው በኋለኞችም ፡ ዘንድ ፡ የሚኖር ፡ ነው የእስራኤል ፡ ፈጣሪ ፡ ቅዱስ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ንጉሥ ፡ ነው ሥልጣን ፡ አለው ፡ ይምራል ፡ ይፈረዳል ፡ ያነሳል ፡ ይሾማል ፡ ያከብራል ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለእርሱ ፡ ይቻላል እግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ይቻለዋል ይራራል ፡ ይወዳል ፡ ይባርካል ይጠራል ፡ ይለያል ፡ ይልካል ከእርሱ ፡ በፊት ፡ አምላክ ፡ አልነበረም ከእርሱ ፡ በኋላም ፡ ማንም ፡ ዓይኖርም እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው የሚያድን ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ያደርጋል ፡ በባሕር ፡ ውስጥ ፡ መንገድን ፡ በኃይለኛ ፡ ውኃ ፡ ውስጥ ፡ መተላለፊያን ይዋጋል ፡ ይረታል ፡ ያሸንፋል በዙፋኑ ፡ ዘለዓለም ፡ ይኖራል