Loading
Singer
አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x) እንደ ፡ ኃጢአት ፡ ብዛት ፡ አልፈረከብኝ እግዚአብሔር ፡ ምህረቱን ፡ አልከለከለኝ በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ምህረት ፡ ባልኩበት ይቅርታ ፡ በዝቶልኝ ፡ ይኸው ፡ ዘመርኩለት አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x) ሊከሱኝ ፡ ወደው ፡ ኃጢአተኛ ፡ ብለው በድንጋይ ፡ ሊወግሩኝ ፡ ዳኛ ፡ ፊት ፡ አቅርበው የተገባኝን ፡ ሞት ፡ አይገባም ፡ ብሎ ምህረት ፡ አረገልኝ ፡ ሀፍረቴን ፡ ከልክሎ አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x) የምህረት ፡ አምላክ ፡ ደጁ ፡ ተከፈተ ለብዙ ፡ በደሌ ፡ ይቅርታ ፡ . (1) . እንደገና ፡ ቆሜ ፡ ፊቱ ፡ ዘምራለሁ የማረኝን ፡ አምላክ ፡ አመሰግናለሁ አዝ፦ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ እንደገና ፡ በብዙ ፡ ይቅርታህ ፡ አከበርከኝ እንደገና ፡ እንደገና ፡ አሄ ፡ እንደገና (፪x)