Loading
Singer
ወደፊት ፡ እንደርሳለን ፡ በአዳዲስ ፡ ምሥጋና ከልባችን ፡ በደስታ ፡ ልንሰግድልህ ፡ እንደገና እያመለክን ፡ ልናመልክህ ፡ እናብዛልህ ፡ ብዙ ፡ ቅኔ ከሃጥያት ፡ ስለፈታኸን ፡ ስለወጣን ፡ ከኩነኔ (፪x) እንደገና (፯x) በአዲስ ፡ ምሥጋና እንደገና (፯x) በአዲስ ፡ ምሥጋና እንደ ፡ ሃጥያታችን ፡ አላደረክብን በበደላችን ፡ መቼ ፡ አጠፋኸን ከቁጣህ ፡ ምሕረትህ ፡ ትቀድማለች ለደካከሙት ፡ ብርታት ፡ ትሆናለች ምሕረትህ ፡ ቸርነትህ ደግነትህ ፡ ርህራሄህ (፪x) ወደፊት ፡ እንደርሳለን ፡ በአዳዲስ ፡ ምሥጋና ከልባችን ፡ በደስታ ፡ ልንሰግድልህ ፡ እንደገና እያመለክን ፡ ልናመልክህ ፡ እናብዛልህ ፡ ብዙ ፡ ቅኔ ከሃጥያት ፡ ስለፈታኸን ፡ ስለወጣን ፡ ከኩነኔ (፪x) እንደገና (፯x) በአዲስ ፡ ምሥጋና እንደገና (፯x) በአዲስ ፡ ምሥጋና ከጥፋት ፡ የታደከን ፡ ከመከራ ቸርነትህ ፡ አያልቅም ፡ ብናወራ ገደብ ፡ የለው ፡ ይቅርታህ ፡ በሕዝብህ ፡ ላይ ምሕረትህ ፡ ከፍ ፡ ያለች ፡ ናት ፡ እስከ ፡ ሰማይ ምሕረትህ ፡ ቸርነትህ ደግነትህ ፡ ርህራሄህ (፬x)