Loading
Singer
አዝ፦ እንደ ፡ ሌባ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ ንጹህ ፡ አምላክ ፡ ሆነልን ፡ ስለእኛ በጨለማ ፡ በድቅድቁ ፡ ሳለን በእግዚአብሔር ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘን (፪x) እጅግ ፡ ከብዶት ፡ ነበረ ፡ መስቀሉ አሸክመው ፡ ሲያስጨንቁት ፡ ዋሉ ለዓለም ፡ ኃጢአት ፡ ኢየሱስ ፡ ተመታ በመስቀል ፡ ሞት ፡ በእርባን ፡ እንዲፈታ (፪x) የደሙ ፡ ላብ ፡ አለዋጋ ፡ አይደለም የጐኑ ፡ ውኃ ፡ ለከንቱ ፡ አልፈሰሰም ንጹህ ፡ ደሙ ፡ ለእንስሳት ፡ አይደለም ክቡር ፡ ማንጻት ፡ አለው ፡ ለእኔም ፡ ለአንተም (፪x) አዝ፦ እንደ ፡ ሌባ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ ንጹህ ፡ አምላክ ፡ ሆነልን ፡ ስለእኛ በጨለማ ፡ በድቅድቁ ፡ ሳለን በእግዚአብሔር ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘን (፪x)