Loading
Singer
እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ አላገኘሁም ብወጣ ፡ ብወርድ ፡ ከቶ ፡ አላየሁም የሚደግፍ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያቆም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ማንን ፡ ጥሎ ፡ እርሱ ፡ ያውቃል ለሚጠሩት ፡ ፈጥኖ ፡ ይደርሳል ጌታ ፡ ብቻ ፡ ለሁሉ ፡ ይበቃል (፪x) እርሱን ፡ የታመነ ፡ በመንገዱ ፡ ሁሉ አይወድቅም ፡ ዘለዓለም ፡ ያቆመዋል ፡ ቃሉ በጨለማው ፡ ዓለም ፡ ብርሃን ፡ እየሆነው ይመራዋል ፡ ጌታ ፡ ቅጥር ፡ እያዘለለው ከጠላት ፡ ተናጥቀህ ፡ ለዚህ ፡ ያበቃኸን ኃይልህንም ፡ ልከህ ፡ እኛን ፡ የረዳኸን በመንገዳችን ፡ ላይ ፡ ቸርነት ፡ አድርገሃል ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል አያስፈልግ ፡ ሌላ ፡ ሁልጊዜ ፡ በቂ ፡ ነህ ዘወትር ፡ ከለላ ፡ ድጋፍ ፡ መመኪያ ፡ ነህ አንተን ፡ የተጠጋህ ፡ የተማጸነህ ፡ ሰው የጠላትን ፡ ሰፈር ፡ አተረማመሰው አመልን ፡ አዋቂ ፡ ገበናን ፡ ሸፋኝ ፡ ነህ አንተ ፡ የናዝሬት ፡ ሰው ፡ ዘወትር ፡ መልካም ፡ ነህ ሁሉን ፡ እንደ ፡ ዓመሉ ፡ ችለህ ፡ ታኖራለህ አትለወጥ ፡ አንተ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ያው ፡ ነህ