Loading
Singer
(እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም) (፪x) እያልኩ ፡ አወራለሁ ፡አወራለሁ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ እይቻለሁ) (፪x) እናቴ ፡ በቅርጫት ፡ ጠቅልላ ፡ ስትጥለኝ ፈርኦንን ፡ ፈርታ ፡ ባሕር ፡ ላይ ፡ ስትተወኝ አግዚአብሄር ፡ እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ አሞቀኝ እንዳልጠፋ ፡ እንዳልሞት ፡ አቅፎ ፡ አተረፈኝ በድንገት ፡ ሳላውቀው ፡ ፈርኦን ፡ ቤት ፡ ገባሁ ምንም ፡ ሳይጐልብኝ ፡ በእናቴ ፡ ጡት ፡ አደኩ እብራይስጥ ፡ እያለሁ ፡ የግብጽ ፡ ይሁን ፡ ተባልኩ በወግ ፡ በመዓረግ ፡ አደኩኝ ፡ በለጽኩ ይህንን ፡ ሁሉ ፡ አለፍኩ ፡ ያን ፡ ሁሉ ፡ አዋቂ ፡ ነው ህዝቡን ፡ አንድመራ ፡ ለካስ ፡ ላላማው ፡ ነው (በልጅነት ፡ ዘመን ፡ ሲመራኝ ፡(ሲያግዘኝ) እያየሁ ማንም ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሆንም ፡ እላለሁ) (፪x) አዝ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ግብጻዊውን ፡ ገድዬ ፡ በረሃ ፡ ስገባ ውኃ ጥም ፡ ሲፈጀኝ ፡ የምበላው ፡ ሳጣ እንዳልተከበርኩኝ ፡ደግሞ ፡ እረኛ ፡ ስሆን ኑሮዬን ፡ ጠልቸው ፡ሳማርር ፡ ጌታዬን ጭራሹን ፡ መጣና ፡ በሽምግልናዬ እግዚአብሄር ፡ ጠራኝ ፡ እኔ ፡ በቃ ፡ ብየ ባደኩበት ፡ ኑሮ ፡ ቤቴ ፡ ተመልሼ ከፈርኦን ፡ ገጠምኩ ፡ በትሬን ፡ በእጄ ፡ ይዤ ለካስ ፡ ለታሬክ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ያስቀመጠኝ ከባሕር ፡ አንስቶ ፡ በቤቱ ፡ ሊሾመኝ (በሽምግልናዬ ፡ ሲመራኝ ፡ሲያግዘኝ) እያየሁ ማንም ፡እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሆንም ፡ እላለሁ) (፪x) አዝ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ይህን ፡ ሁሉ ፡ አለፍኩ ፡ ያን ፡ ሁሉ ፡ አዋቂ ፡ ነው ህዝቡን ፡ እንድመራ ፡ ለካስ ፡ ለአላማው ፡ ነው በልጅነት ፡ ዘመን ፡ ሲመራኝ ፡ እያየሁ ማንም ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሁንም ፡ እላለሁ ለካስ ፡ ለታሬክ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ያስቀመጠኝ ከባሕር ፡ አንስቶ ፡ በቤቱ ፡ ሊሾመኝ (በሽምግልናዬ ፡ ሲመራኝ ፡ሲያግዘኝ) እያየሁ ማንም ፡እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሆንም ፡ እላለሁ) (፪x) አዝ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ