Loading
Singer
ኦሆሆ ፡ አምላኬም ፡ ቢናገር ፡ ቢል ፡ እንደኔ ፡ ማን ፡ ነው እውነተኛነቱን ፡ እራሱን ፡ ቢያውቀው ፡ ነው የሚያመልኩት ፡ ሁሉ ፡ ቢሉ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ማን ፡ ነው መልካም ፡ አገዛዙን ፡ ፅድቁን ፡ ቀምሰውት ፡ ነው እኔ ፡ እላለሁ (፫x) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማን ፡ ነው እንደ ፡ አምላኬ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ ነው ማን ፡ ነው (፫x) አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x) ቁመተ ፡ ረዥም ፡ ሰፊ ፡ ትከሻ ለንጉሥነት ፡ አምላክ ፡ የሚሻ መሰለውና ፡ ተንጐራደደ እኔ ፡ ነኝ ፡ ብቁ ፡ ብሎ ፡ ፈረደ አምላኬ ፡ መቼ ፡ ሊያይ ፡ እንደ ፡ ሰው የፊት ፡ የፊቱን ፡ ከላይ ፡ ያለው እርሱ ፡ ወደ ፡ ውስጥ ፡ አጥርቶ ፡ ያያል ልበ ፡ ቀናውን ፡ መርጦ ፡ ይሾማል ቢረሳም ፡ እንኳን ፡ በሰዎች ፡ ከቶ በጌታ ፡ ፊት ፡ ግን ፡ ይታያል ፡ ጐልቶ ዳዊት ፡ ትንሹ ፡ ተጠርቶ ፡ መጣ ከታች ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ በቅባት ፡ ወጣ ተንበሸበሽ ፡ በተስፋ ፡ ቃል ነገ ፡ በእስራኤል ፡ ንጉሥ ፡ ሊባል የተረሳውን ፡ የሚያይ ፡ አምላክ ለዘለዓለም ፡ ሥሙ ፡ ይባረክ አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x) ቢዶሉትብህ ፡ ቢመካከሩ በጥልቅ ፡ ጉድጓድ ፡ አንተን ፡ ሊቀብሩ ሞተሃል ፡ ብለው ፡ ቢነዙ ፡ ወሬ በዱር ፡ ሰጠመ ፡ ተበላ ፡ በአውሬ ሕልም ፡ አሳይቶ ፡ ተስፋ ፡ ሰጥቶሃል ለነፍሰ ፡ ገዳይ ፡ መች ፡ ይሰጥሃል በአሕዛብ ፡ ምድር ፡ ብትሰደድም የያዝከው ፡ ተስፋ ፡ መሆኑ ፡ አይቀርም በግብጽ ፡ ምድር ፡ ብትሆን ፡ ግዞት የተነገረህ ፡ ቃሉ ፡ እርሱ ፡ አይሞት ጊዜን ፡ ጠብቆ ፡ ይከናወናል አሳዳጆችህ ፡ ይሰግዱልሃል ቢመስልም ፡ ነገር ፡ የተጓተተ የሌላው ፡ ሚስጥር ፡ ሲፈታ ፡ በአንተ በተጣልክበት ፡ አብሮ ፡ የሆነው የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x) ሀማ ፡ ቢፎክር ፡ ቢያኖር ፡ መስቀያ አንተ ፡ ግን ፡ ዘምር ፡ በኃሌሉያ ሲያልፍ ፡ ሲያገድም ፡ ቁጭ ፡ በል ፡ በፊቱ የእጁን ፡ ልትቀማው ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ ንጉሡ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ይቀሰቀሳል መዝገብን ፡ ይዞ ፡ ያገላብጣል ያን ፡ ጊዜ ፡ ነገር ፡ ይለዋወጣል ሹሙት ፡ አንግሡ ፡ ቀቡት ፡ ይባላል አምላክህ ፡ ፃዲቅ ፡ ፈራጂ ፡ ነውና ሳትደናገጥ ፡ ጠብቅ ፡ ቁምና በፊትህ ፡ መውደቅ ፡ የጀመረው ፈጽሞ ፡ ይወድቃል ፡ ድል ፡ የአንተ ፡ ነው በአንተ ፡ ጀምሮ ፡ በአንተ ፡ ይፈጽማል የአይሁድ ፡ መዳን ፡ ይረጋገጣል መርደኪዮስ ፡ ሆይ ፡ አባክህ ፡ ፅና የጌታን ፡ ክብር ፡ ልታይ ፡ ነውና አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x)