Loading
Singer
ሰው ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ ፡ ይከዳል ጊዜን ፡ ጠብቆ ፡ ይርቃል ተስፋ ፡ እንደሌለው ፡ የማይተው ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው ዕውቀትን ፡ አይቶ ፡ ይከዳል አላፊ ፡ መሆኑን ፡ ዘንግቷል እያየ ፡ የአሁን ፡ የአሁኑን ረስቶ ፡ አወዳደቄን አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x) ዘለዓለም (፪x) ትካዜዬን ፡ ለእርሱ ፡ ጥዬ የውስጤን ፡ መቃተት ፡ ጌታዬ ሰው ፡ እንኳን ፡ ቢከዳ ፡ ቢጥል እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ይረዳል ሃሳቤን ፡ የሚያውቅልኝ ድካሜን ፡ የሚረዳልኝ የውስጥ ፡ ጭንቀቴ ፡ የሚገባው እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው? አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x) ዘለዓለም (፪x) አጽናኝ ፡ መስሎ ፡ ይጠጋል ጓደኛ ፡ መስሎ ፡ ይቀርባል ጠላትም ፡ በእርሱ ፡ ተጠቅሞ ብርሃኔንም ፡ አጨልሞ ግን ፡ የሚመካው ፡ የምጠጋው የልቤን ፡ የማጫውተው ድጋፍ ፡ መከታ ፡ የማደርገው እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው? አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x) ዘለዓለም (፪x)