Loading
Singer
አዝ፦ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚቆም ፡ ከጐኔ የልቤን ፡ ተረድቶ ፡ እንባ ፡ የሚያብስ ፡ ከዓይኔ (፪x) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x) ትናንትና ፡ እንዴት ፡ ይታለፍ ጭንቅ ፡ ነበር ፡ ለብቻ ፡ ሲታሰብ በዙሪያዬ ፡ ጠላት ፡ ከቦኝ ማን ፡ ያድነኝ ፡ ብዬ ፡ ተረበሽኩኝ ሰማያት ፡ ተከፈቱና በተከበበው ፡ ከተማ ምህረቱን ፡ አበዛልኛ (፪x) ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነህ (፮x) አዝ፦ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚቆም ፡ ከጐኔ የልቤን ፡ ተረድቶ ፡ እንባ ፡ የሚያብስ ፡ ከዓይኔ (፪x) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x) ስደክምበት ፡ ዞር ፡ በይ ፡ ደካማ አላለኝ ፡ ደግ ፡ ነው ፡ ጌታ አቅም ፡ ሆነ ፡ ኃይል ፡ አስታጠቀኝ በከፍታ ፡ ላይ ፡ አቆመኝ ሰማያት ፡ ተከፈቱና በተከበበው ፡ ከተማ ምህረቱን ፡ አበዛልኛ (፪x) ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነህ (፮x)