Loading
Singer
የአማልክት ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ የነገስታት ፡ ንጉስ የሚመስልህ ፡ የሌለህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ እየሱስ አመልክሃለሁ/4X/ መጥቻለሁ ፡ በፊትህ ፡ ላመልክህ ፡ ነው አስቀድሜ ፡ በእግርህ ፡ ስር ፡ እሰግዳለው ቀና ፡ ብዬ ፡ አንተን ፡ ሳይ ፡ ተውበሃል የምስጋናን ፡ የክብርን ፡ ዘውድ ፡ ጭነሃል እጨምራለው ፡ በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ንጉሴ ፡ ሆይ ከዚህም ፡ በላይ ፡ ንገስ ፡ ባማረ ፡ ዜማ በተዋበ ፡ እልልታ ፡ ይድመቅ ፡ ዙፋንህ ተመለክ ፡ ተውደስ ፡ የኔ ፡ ጌታ እኔም ፡ አላውቅህም ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ሆነ ፡ ማንነትህ /2X/ ከፍ ፡ ባለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ የተቀመጥቀው ብርሃንን ፡ እንደ ፡ ልብስ ፡ የለበስከው ማዕረግህ ፡ ስልጣንህ ፡ የብቻህ ፡ ነው በሹመትስ ፡ የተሾመ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው እጨምራለው ፡ በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ንጉሴ ፡ ሆይ ከዚህም ፡ በላይ ፡ ንገስ ፡ ባማረ ፡ ዜማ በተዋበ ፡ እልልታ ፡ ይድመቅ ፡ ዙፋንህ ተመለክ ፡ ተውደስ ፡ የኔ ፡ ጌታ እኔም ፡ አላውቅህም ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ሆነ ፡ ማንነትህ /2X/ በክብር ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ክቡር ፡ ማነው ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው በሞገስ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ሞገሳም ፡ ማነው ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው በሀይል ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ሀያል ፡ ማነው ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው በስልጣን ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ባለስልጣን ፡ ማነው ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው በአማልክት ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ አምላክ ፡ ማነው ኧረ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው በፍጹም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም/2X/ አይኖርም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም/2X/