Loading
Singer
አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ ኦ ፡ መዳኔ ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል የፍቅርህ ፡ ብዛቱ ፡ እንዲህ ፡ ያዘምረኛል ውለታህ ፡ መች ፡ ዝም ፡ ያሰኛል (፫x) ላውራ ፡ ማዳንህን ፡ ጌታ ላውራ ፡ ስራህን ፡ ኢየሱስ (፪x) ተስፋ ፡ ቆርጬ ፡ ሌት ፡ ቀን ፡ ሳነባ መድረሻ ፡ ጠፍቶኝ ፡ ሆኜ ፡ እምባ ፡ በእምባ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ የደረሰልኝ እምባዬን ፡ ጠርጐ ፡ ና ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ ያለኝ አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ ጐልያድ ፡ በፊቴ ፡ እንዲያው ፡ ተደንቅሮ ባስጨነቀኝ ፡ ቁጥር ፡ ሳሰማ ፡ እሮሮ ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ከተፍ ፡ ያለልኝ ያንን ፡ ተራራውን ፡ ከፊቴ ፡ ጣለልኝ አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ጠራሁህ መታመኛዬ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነህ ፡ አልኩህ አንተም ፡ አልናከኝም ፡ ቃሌን ፡ ሁሉ ፡ ሰማህ ምሥጋና ፡ ውዳሴ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ ኦ ፡ መዳኔ ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል የፍቅርህ ፡ ብዛቱ ፡ እንዲህ ፡ ያዘምረኛል ውለታህ ፡ መች ፡ ዝም ፡ ያሰኛል (፫x) ላውራ ፡ ማዳንህን ፡ ጌታ ላውራ ፡ ስራህን ፡ ኢየሱስ (፪x)