Loading
Singer
ጌታ ፡ ሆይ ፡ በጐነትህንና ፡ ቸርነትህን ፡ መልካምነትህንና ፡ ፍቅርህን ፡ አይቼ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ እንደሌለ ፡ ተረድቼ ፡ ልከተልህ ፡ ወሰንኩ አዝ:- እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x) በድዬና ፡ እጥፍቼ ፡ ሳለሁ ፡ ካንተ ፡ ርቄ (፪x) በምህረት ፡ አየኸኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ (፪x) ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ምክንያት ፡ የማይፈልግ (፪x) እንዲሁ ፡ የሚያፈቅር ፡ በዳዩን ፡ የሚወድ (፪x) አዝ:- መንፈስ ፡ ቅዱስ (፬x) እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x) ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ ላማ ፡ ሰበቅታኒ ፡ ብሎ ፡ ሞተ ፡ ለኛ ለእኔ ፡ ብሎ ፡ ነው ፡ መቃብር ፡ የተኛ (፪x) አዝ:- ኢየሱሴዋ (፬x) እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x) ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፬x)