Loading
Singer
አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x) በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ ፍፁም ፡ ፈውስም ፡ በእጅህ ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ! እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x) ቤቴስ ፡ ምንድነው ? የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ በአንተ ፡ አገኘሁ ጌታ ፡ ተመስገን ! ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆኗል ከእኔ ፡ የሆነ ፡ የለም አንተን ፡ የታመነ ፡ መች ፡ ወድቋል? ዘለዓለም ፡ በጥላህ ፡ ይኖራል በምትችለው ፡ በአንተ ፡ መመካት ይሻላል ፣ ይጠቅማል ፡ መኩራራት ! ተነሣሁ ፡ ከአመድ ፡ ከትቢያ ረዳኸኝ ፡ አንተ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ! የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰልኝ ! ስምህን ፡ ለማክበር ፡ በቃሁኝ ! አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x) በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ ፍፁም ፡ ፈውሥም ፡ በእጅህ ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ! እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x) ቤቴስ ፡ ምንድነው ? ቅጥርን ፡ ማዘለል ፣ ማበርታት ፡ ታውቃለህ ለደካማው ፡ ኃይልን ፣ ብርታት ፡ ትሰጣለህ ማለዳ ፣ ማለዳ ፡ ኃይልህን በመከራ ፡ ጊዜ ፣ ማዳንህ የማይዘነጋ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ የየቀኑ ፡ ታላቅ ፡ ምክርህ አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x) በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ ፍፁም ፡ ፈውሥም ፡ በእጅህ ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ! እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x) ቤቴስ ፡ ምንድነው ? ያደረግኸው ፡ ለእኔ ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው ጌታ ፡ ተመስገን ! የውለታህም ፡ ልክ ፡ ከምለው ፡ በላይ ፡ ነው እጅህ ፡ የማይደክም ፡ ሁልጊዜ ጽኑ ፡ መከታ ፡ ነህ ፡ ለነፍሴ ማረፍ ፡ በአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ዘወትር ፡ ስምህን ፡ ማክበር ፡ ነው አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x) በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ ፍፁም ፡ ፈውሥም ፡ በእጅህ ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ! እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x) ቤቴስ ፡ ምንድነው ?