Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ይሳነዋል እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ያቅተዋል የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ታድሶ እምባችን ፡ ከዓይናችን ፡ ታብሶ (፪x) እናያለን ፡ እናያለን ፡ እናያለን በነቢያቱ ፡ አፍ ፡ የተነገረው የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን (፪x) በእግዚአብሔር ፡ ሰዎች ፡ የተባለውን የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን የወደቀችውን ፡ የዳዊትን ፡ ድንኳን ፡ አነሳለሁ ፡ ያለ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ይችላል ፡ ንጉሡ የቀድሞውን ፡ ግብር ፡ በእጥፍ ፡ እንዲመልስ ፡ በእራሱ ፡ የማለ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ይችላል ፡ ንጉሡ (፪x) ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱ (ይችላል ፡ ንጉሡ) (፬x) ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x) የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መሰዊያው ፡ ፈረሰ ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x) የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መርገጫው ፡ ፈረሰ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ይሳነዋል እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ ይሰራል ፡ ምንስ ፡ ያቅተዋል የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ታድሶ እምባችን ፡ ከዓይናችን ፡ ታብሶ (፪x) እናያለን ፡ እናያለን ፡ እናያለን በነቢያቱ ፡ አፍ ፡ የተነገረው የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን (፪x) በእግዚአብሔር ፡ ሰዎች ፡ የተባለውን የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ እንወርሳለን የገሃነም ፡ ደጆች ፡ የማይቋቋሟት ፡ ታላቅ ፡ የቀደሳት/የመረጣት ንጉሧ ፡ ነግሶ ፡ ሲገለጥባት ዝናዋ ፡ ሞገሷ ፡ ከዳር ፡ ዳር ፡ ሲወጣ ፡ ስትሆን ፡ ገናና ይህን ፡ በዓይናችን ፡ እናያለን ፡ ገና (፪x) ዝማሬ ፡ ገኖ (እናያለን ፡ ገና) ምድርን ፡ ሲሞላ (እናያለን ፡ ገና) ተስፋን ፡ የሰጠው (እናያለን ፡ ገና) ታማኝ ፡ ነውና (እናያለን ፡ ገና) ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x) የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መሰዊያው ፡ ፈረሰ ምርኮ ፡ ተመለሰ ፡ ተመለሰ (፪x) የጠላት ፡ መቆሚያ ፡ መርገጫው ፡ ፈረሰ ገና ፡ ገና ፡ እናያለን ፡ ገና...