Loading
Singer
እናምናለን ፡ እናምናለን እኛም ፡ ተጐብኝተን ፡ እናያለን እናምናለን ፡ እናምናለን የእግዚአብሔርን ፡ ክብር ፡ እናያለን እናምናለን ፡ እናምናለን ኢትዮጵያም ፡ ተጐብኝታ ፡ እናያለን እናምናለን ፡ እናምናለን አዲስን ፡ ነገር ፡ እናያለን የመጐብኛችን ፡ ቀን ፡ ደርሶ የእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ከላይ ፡ ወርዶ ልመናዋ ፡ ተሰምቶላት ለቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ . (1) . እናያለን ፡ ገና ፡ በጌታ ጥማት ፡ ተለውጦ ፡ በእርካታ እናያለን ፡ ብዙ ፡ በጌታ ያስለቀሰን ፡ ሁሉ ፡ ሲመታ እናምናለን ፡ እናምናለን ስድባችን ፡ ተወግዶ ፡ እናያለን እናምናለን ፡ እናምናለን ፀሎት ፡ ተመልሶ ፡ እናያለን ለሰዎች ፡ ጥያቄ ፡ ሆነን እስከ ፡ መቼ ፡ እንኖራለን በስውር ፡ የለመንነውን በግልፅ ፡ እንቀበላለን መቼ ፡ እንዳለቀሰች ፡ ትቀራለች ሃናም ፡ ሳሙኤልን ፡ ትወልዳለች መቼ ፡ እንዳለቀሰች ፡ ትቀራለች ሣራም ፡ ይስሐቅን ፡ ትወልዳለች እናምናለን ፡ እናምናለን መካኒቱ ፡ ወልዳ ፡ እናያለን እናምናለን ፡ እናምናለን አዲስን ፡ ነገር ፡ እናያለን የእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ሲገለጥ ማነው ፡ በፊቱ ፡ የሚቆመው አጋንንት ፡ ኃጢአት ፡ በሽታ ይወገዳሉ ፡ ፈፅመው የታሰሩት ፡ ሁሉ ፡ ይፈታሉ ለአምላካቸው ፡ ክብርን ፡ ይሰጣሉ አመፀኞች ፡ ሁሉ ፡ ይማረካሉ ለኢየሱሴ ፡ ክብር ፡ ይሰግዳሉ እኔ ፡ እናምናለሁ ፡ እኔ ፡ እናምናለሁ የጌታን ፡ ተዓምራት ፡ አያለሁ እኔ ፡ እናምናለሁ ፡ እኔ ፡ እናምናለሁ ገና ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ ጠላቴ ፡ ቢገለኝ ፡ ሁሌ ፡ ቢፈልገኝም ዛሬም ፡ በሕይወት ፡ አለሁ ፡ ከቶ ፡ አላገኘኝም በቀረው ፡ ዘመን ፡ ወዴት ፡ ያገኘኛል ገና ፡ እንደምኖር ፡ ጌታ ፡ ተናግሮኛል በቀረው ፡ ዘመን ፡ ወዴት ፡ ያገኘኛል እንደማገለግል ፡ ጌታ ፡ ተናግሮኛል አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ ገና ፡ ዘምራለሁ አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ የኢየሱሴን ፡ ሥራ ፡ ገና ፡ እሰራለሁ ገና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ አስፈልገዋለሁ በጨለማ ፡ ላሉ ፡ ብርሃን ፡ ሆናለው መከሩ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ብዙ ፡ ነፍስ/ሰው ፡ ይድናል በሕይወት ፡ እያለሁ ፡ ተስፋው ፡ ይፈፀማል (፪x) አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ የዲያቢሎስን ፡ ሥራ ፡ ገና ፡ አፈርሳለሁ ባለፈው ፡ ዘመኔ ፡ ምንም ፡ ብበድለው የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ እንው በማልጠቅመው ፡ በኩን ፡ ሥራውን ፡ ይሰራል ደስ ፡ አሰኘዋለሁ ፡ በእኔው/በልጁ ፡ ይከብራል (፪x) አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ በእግዚአብሔር ፡ ፀጋ ፡ አገለግላለሁ አልሞትም ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ እለመልማለሁ