Loading
Singer
አዝ:- ብዙዎች ፡ እንደፈለጋቸው አንተንም ፡ ሳይፈሩ ፡ የሚኖሩ ፡ ናቸው ሲላቸው ፡ እንደምኞታቸው ፡ ቃልህን ፡ ይገልጻሉ እራሳቸው ፡ ስተው ፡ ሌላውን ፡ ያስታሉ አሉ ፡ ደግሞ ፡ ጥቂት ፡ አንተን ፡ የሚፈሩ ምህረትህን ፡ ታምነው ፡ በጽድቅ ፡ የሚኖሩ ታጋሽ ፡ ቸር ፡ ሩህሩህ ፡ ምህረትህ ፡ የበዛ ለእነሱ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ ጨካኝ ፡ ከተቆጣ እኔ ፡ ከእነዚህ ፡ ጋር ፡ ፈጥኜ ፡ እስማማለሁ ላለፈው ፡ በደሌ ፡ ንስሃ ፡ እገባለሁ ድንገት ፡ ሳትጥለኝ ፡ ዛሬ ፡ እመለሳለሁ እመለሳለሁ ፡ ፍሬም ፡ ማያፈራ ፡ የደረቀ ፡ እንጨት ማይጠቅም ፡ ዛፍ ፡ ተቆርጦ ፡ መጣል ፡ ነው ፡ በማይጠፋው ፡ እሳት ልትመጣ ፡ ነው ፡ ክብርህን ፡ ልትገልጥ ፡ ቤትህን ፡ ልታጠራ ኀጢአት ፡ ልትቀጥፍ ፡ ጅራፍህን ፡ ይዘህ ፡ ተነስተሃልና አይሆንም ፡ ብሎ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን ፡ የሚከለክልህ እንዴ ፡ ከያዝከኝ ፡ የትኛው ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ከእጅህ ፡ የሚያስጥለኝ እመለሳለሁ ፡ የኔ ፡ መጨረሻ ፡ የኔ ፡ እድል ፡ ፈንታዬ እመለሳለሁ ፡ እንደ ፡ እንጨቱ ፡ እንዳይሆን ፡ መልሰኝ ፡ ጌታዬ መልሰኝ ፡ ጌታዬ ፡ መልሰኝ አዝ:- ብዙዎች ፡ እንደፈለጋቸው አንተንም ፡ ሳይፈሩ ፡ የሚኖሩ ፡ ናቸው ሲላቸው ፡ እንደምኞታቸው ፡ ቃልህን ፡ ይገልጻሉ/ይጠቅሳሉ እራሳቸው ፡ ስተው ፡ ሌላውን ፡ ያስታሉ (፬x)