Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ ለቤቱ ፡ ቀንቷል ጠላትን ፡ ያዋርዳል ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይበሏታል ነብያትን ፡ ይታደጋል ፡ አያይአሃ ከእጆችዋም ፡ ያስመልጣል ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይበሏታል አዝ፦ ማነው ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ የሚበቀላት ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x) ቀድማ ፡ እራሷን ፡ አስጊጣ ፡ አለች ፡ ሰውን ፡ ልታስት ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x) መሸነፍ ፡ ከእንግዲህ ፡ ያብቃ ፡ ዛቻዋን ፡ ሰምቶ ፡ ድበቃ ውጣና ፡ ተበቀላት ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይብሏት መሸነፍ ፡ ከእንግዲህ ፡ ያብቃ ፡ ዛቻዋን ፡ ሰምቶ ፡ ድበቃ ውጪና ፡ ተበቀያት ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይብሏት አዝ፦ ማነው ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ የሚበቀላት ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x) ቀድማ ፡ እራሷን ፡ አስጊጣ ፡ አለች ፡ ሰውን ፡ ልታስት ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x) የተኛህ ፡ ንቃ ፡ ቀን ፡ ሳለ እሷ ፡ እያለች ፡ ምን ፡ ሰላም ፡ አለ አብረን ፡ እናስወግዳት አስጥላት ፡ እንዳታነሳት እኔ ፡ ባለሁበት ፡ ከተማ አይሰራም ፡ ግልሙትናዋ እኛም ፡ ባለንበት ፡ መንደር አይሰልጥን ፡ የእሷ ፡ ነገር