Loading
Singer
ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ወዳእላዕፋት ወደ በኩራት ማህበር እሱ ከመረጠኝ ክብሩን እንድናገር ላመስግነው እንጂ ሌላ ምን እላለሁ የወደደኝ ጌታን ከፍ አደርገዋለሁ ጌታ ነው ልበለው ጌታ ነው ×2 ልዩ ነው ልበለው ልዩ ነው ×2 ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2 ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2 ገናና ነው እግዚአብሔር ×2 ገናና ነው እግዚአብሔር ×2 1.በባርነት ቀንበር ውስጥ ተጎሳቁዬ ሳለሁ ከሞት መንገድ መልሶኝ በብርሀኑ ብርሀን አየሁ አሁን ማንም አያውቀኝ በቀደመው ታሪኬ በመስቀል ጠርቆታል የወደደኝ አምላኬ ታሪኬም ኑሮዬም ተቀየረ በቃ ×2 ጠላቴ መሸበት ለኔ ሌቱ ነጋ ×2 ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2 ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2 ገናና ነው እግዚአብሔር ×2 ገናና ነው እግዚአብሔር ×2 2 .ፋሬስ ይሁን አለና አምላኬ አስጥሶኛል ብዙ ኋለኛ ሳለሁ ፊተኛ አድርጎኛል ስራዬን ሁሉ ሰርቶ ጎዳናዬን አቅንቷል እግዚአብሔር መሐሪ ነው ፊቱን ለኔ አብርቷል አዝማች ......... 3. ሰው መሆኔ በእርሱ ነው ህይወቴም ያማረልኝ ትቢያዬን ሁሉ አራግፎ ባለ ማዕረግ ያረገኝ አላፍርበት ባወራው ጌታ የሰራልኝን የከፋው ይክፋው እንጂ እግዚአብሔር ይክበርልኝ ታሪኬም ኑሮዬም ተቀየረ በቃ ×2 ጠላቴ መሸበት ለኔ ሌቱ ነጋ ×2 ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ገናና ነው እግዚአብሔር ገናና ነው እግዚአብሔር አዶናይ ነው እግዚአብሔር ሰላሜ ነው እግዚአብሔር ሞገሴ ነው እግዚአብሔር እረፍቴ ነው እግዚአብሔር