Loading
Singer
መክፈት፡አይችልም፡ወይ ቁልፉ፡በእጁ፡አይደለም፡ወይ፡(፪×) ኧረ፡ይችላል፡ኧረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡ ማክበር፡አይችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አይደለም፡ሆይ፡(፪×) ኧረ፡ይችላል፡ኧረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡ ማገዝ፡አችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አይደለም፡ሆይ(፪×) ኧረ፡ይችላል፡ኧረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡ ይችላል፡ያደርጋል፡ተወራርጃለሁ፡ ነገሬን፡ሰርቶልኝ፡እኔማ፡አይቻለሁ፡ ይኸዉ፡ተገርሜ፡እዘምራለሁ፡ ይኸዉ፡ተደንቄ፡እዘምራለሁ፡(፪×) 1በነቢያት፡መንፈስ፡እኔ፡እናገራለሁ፡ በሞተዉ፡ነገር፡ላይ፡ ትንሳዔ፡አወራለሁ፡ የደረቁ፡አጥንቶች፡የተበታተኑ፡ ትንቢቱ፡ሲመጣ፡ሰራዊቶች፡ሆኑ፡ ዛሬም፡ይሰራል፡ይሰራል፡ቃሉ፡ይፈጥራል፡ይፈጥራል፡የሌለን፡ነገር፡ያመጣል፡(፪×) ዕድሜ፡ቀጥሎ፡ኑር፡አለኝና፡ዘማሬ፡ሰጥቶ፡ሞላኝ፡ምስጋና፡ ዕልልታ፡ሆኗል፡ መታወቂያዬ፡ሞልቶ፡ይፈሳል፡ሐሴት፡ደስታዬ፡ ምድረበዳዉን፡ኤደን፡በረሐዉ፡ንገነት፡አደረገዉ፡አሀ፡ቀያየረና፡አሀ፡አደረገዉ፡ ከዓለቱ፡ላይ፡ምንጭን፡አፍልቆ፡አጠጣዉ፡ለተጠማዉ፡አሀ፡ተአምር፡ሰራና፡አሀ፡ለተጠማዉ ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከሁኔታዎች፡በላይ፡ ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከኃያላኖች፡በላይ፡ ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ…………………. መክፈት፡አይችልም፡ወይ ቁልፉ፡በእጁ፡አይደለም፡ወይ፡(፪×) ኧረ፡ይችላል፡ኧረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡ ማክበር፡አይችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አይደለም፡ሆይ፡(፪×) ኧረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡ ማገዝ፡አችልም፡ወይ፡ሥልጣን፡የእርሱ፡አይደለም፡ሆይ(፪×) ኧረ፡ይችላል፡ኸረ፡ይችላል፡እንደ፡እኔ፡ያየ፡ይመሰክራል፡ ይችላል፡ያደርጋል፡ተወራርጃለሁ፡ ነገሬን፡ሰርቶልኝ፡እኔማ፡አይቻለሁ፡ ይኸዉ፡ተገርሜ፡እዘምራለሁ፡ ይኸዉ፡ተደንቄ፡እዘምራለሁ፡(፪×) 2፡-አላሳልፍ፡ያለኝ፡የብረቱ፡መዘጊያ፡አዉቆ፡ተከፈተ፡ ሆነልኝ፡ማለፊያ፡እግ/ር፡መንገዴን፡ቀና፡ካደረገዉ ከፍ፡ከፍ፡እንዳልል፡ከልካይ፡እረ ማነዉ፡ ሂድ፡ተከናወን፡ብሎኛል፡ዉጣና፡ዉረስ፡ብሎኛል፡አዝማቼ፡ከፊቴ፡ቀድሟል፡፪× ሕልም፡ብዬ፡የነገርኳቸዉ፡የማይፈፀም፡ቅዠት፡መስሏቸዉ፡ ያንን፡ሕልመኛ፡እንየዉ፡ሲሉ፡ጌታም፡ታማኝ፡ነዉ፡መጣ፡እንደ፡ቃሉ፡ ወደ፡ሹመት፡ስፍራ፡መፃተኛዉን፡ሰዉ፡አፈጠነዉ፡አሀ፡አሰቸኮለና፡አሀ፡አፈጠነዉ፡ ወገን፡በሌለበት፡በባእድ፡ምድር፡ላያ፡አነገሰዉ፡ሸላለመና፡አነገሰዉ፡ ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከሹማምንቶች፡በላይ፡ ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ፡ከመኳንንቶች፡በላይ፡ ኤልሻዳይ፡ኤልሻዳይ………………….