Loading
Singer
በሳር ፡ ብንሰራ ፡ ባገዳ ተቃጥሎብን ፡ እንዳንጎዳ የሚያነጥር ፡ እሳት ፡ ሲመጣ ማነው ፡ ተፈትኖ ፡ ሚወጣ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር የተናገርኩትን ፡ እንድኖር እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን (፪x) በጨለማ ፡ የተሰወረ ፡ በማስመሰል ፡ ኑሮ ፡ የኖረ ወደ ፡ ብርሀን ፡ ታወጣለህ ለሁሉም ፡ እንደስራው ፡ ትሰጣለህ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር የተናገርኩትን ፡ እንድኖር እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን (፪x) አንዳንዱ ፡ ለደሞዝ ፡ ይሰብካል ሌላኛው ፡ ለጥቅም ፡ ያመልካል ታዲያ ፡ ማነው ፡ አንተን ፡ ፈላጊ የተናገረውን ፡ አድራጊ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር የተናገርኩትን ፡ እንድኖር እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን (፪x) ባፌ ፡ ብዙ ፡ ፍቅርን ፡ ስገልጥ ወንድሜን ፡ በነገር ፡ ስረግጥ ቃል ፡ አባይ ፡ ሆኜ ፡ እንዳልገኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሀሰት ፡ ጠብቀኝ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር የተናገርኩትን ፡ እንድኖር እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን (፪x) በጓዳም ፡ ይሁን ፡ በጎዳና ነውር ፡ የሌለባት ፡ ህሊና በእግዚአብሄርና ፡ በሰው ፡ ፊት እንድራመድ ፡ እርዳኝ ፡ በእውነት